በምስራቅ ወለጋ ዞን በአንገር ጉትን ከተማ የብርጋዲዬር ጀነራል አሳምነው ፅጌን ፎቶ የታተመበት ቲሸርት የለበሰው ወጣት በኦሮሚያ ልዩ ሐይል ክፉኛ ተደበደበ! አሁንም በእስር ላይ ይገኛል ሲሉ…

በምስራቅ ወለጋ ዞን በአንገር ጉትን ከተማ የብርጋዲዬር ጀነራል አሳምነው ፅጌን ፎቶ የታተመበት ቲሸርት የለበሰው ወጣት በኦሮሚያ ልዩ ሐይል ክፉኛ ተደበደበ! አሁንም በእስር ላይ ይገኛል ሲሉ የአይን እማኞች ገለጹ። ሰ.አሜሪካ:- ሰኔ 21/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ በአንገር ጉትን ከተማ የአሳምነው ጽጌን ቲሸርት የለበሰው ወጣት በኦሮሚያ ልዩ ሐይል ተደበደበ። በአንገር ጉትን በአዱኛ ኤጎ የሚመራው የሚመራው ልዩ ሐይል በከተማዋ አረጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ያለበት መልበስ እንደወንጀል ያስቆጥራል ያሳሳስራል ብሏል። ከድብደባው የተረፈው ወጣት በልዩ ሐይሉ ካምፕ በማዘጋጃ ውስጥ በእስር ላይ ይገኛል:: በትናንትናው እለት ጋቸና ሲርና ወይም የስርዓቱ ጋሻ የተባሉትን የአንገር ጉትን አስተዳደር ሰብስቦ ለማወያየት ሞክሮ ነበር። በውይይቱ የተሳተፉ በርካታ የስርዓቱ ጋሻ ተብለው የሰለጠኑት ግን ጥያቄያቸውን መመለስ ቀርቶ ቀና ብሎ ተስኖታል ተባለ። በዋሴ አስተዳደር በፌዴራል መንግስት ትዕዛዝ ስልጠና የተሰጡት እነዚህ ወጣቶች አንድም መሳሪያ አላገኙም። ነገርግን በብሔር ለይተው በሶስተኛ ዙር ለሰለጠኑት ሙሉ መሳሪያ ተሰጥተዋል:: ስለሆነም እኛ የአንገር ጉትን የስርዓቱ ጋሻ በባዶ እጃችን የምንጠብቅበት አንዳች ምክንያት የለም ብለዋል። ©የ አንገር ጉትን ነዋሪ #በቃ! #እምቢ! #AmharaGenocide! ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply