You are currently viewing #በምስራቅ ወለጋ ዞን በጉበሰዮ ወረዳ በአኖ ከተማ በዛሬው ዕለት በርካታ ያማራ ተወላጆች መጨፍጨፋቸው ተገለፀ! ጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ጥር 25/2015 ዓ/ም የኦሮሚያ ል…

#በምስራቅ ወለጋ ዞን በጉበሰዮ ወረዳ በአኖ ከተማ በዛሬው ዕለት በርካታ ያማራ ተወላጆች መጨፍጨፋቸው ተገለፀ! ጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ጥር 25/2015 ዓ/ም የኦሮሚያ ል…

#በምስራቅ ወለጋ ዞን በጉበሰዮ ወረዳ በአኖ ከተማ በዛሬው ዕለት በርካታ ያማራ ተወላጆች መጨፍጨፋቸው ተገለፀ! ጥር 25 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ጥር 25/2015 ዓ/ም የኦሮሚያ ልዩሃይል እና ግብራበሮቹ በከፈቱት ተኩስ በርካታ አማራዎች መጨፍጨፋቸውን ምንጮቻችን ለአሻራ ሚድያ ተናግረዋል። ታጣቂዎቹ ዛሬ ጥዋት 11 ሰዓት ጀምረው በከፈቱት ጥቃት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካታ አማሮች የተገደሉ ሲሆን አሸባሪወቹ የአማራ የሆኑ ሃብት ንብረቶችንም ዘርፈዋል ነው የተባለው። በመንግስት አካላት የሚደገፈው መቋጫ ያልተገኘለት የወለጋው የዘር ፍጅት ዛሬ እንደ አዲስ በተከፈተው ጭፍጨፋ በርካቶች ተገድለዋል። የአኖ ከተማን በቁጥጥር ስር አስገብተው በከተማዋ እንዳሻቸው እየፈነጩ እንደሚገኙም ተረጋግጧል። በመንግስት ይሁንታ እየተጨፈጨፈ ያለው የአማራ ህዝብ በተለይም በወለጋ ምድር የአማራ ሞት እየተለመደ በመምጣቱ የሚደርስብን ግፍ እና በደል ተባብሶ ቀጥሏል ብለዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply