በምስራቅ ወለጋ ዞን በጊዳ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ በርካታ አማራዎች መገደላቸውና መፈናቀላቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም…

በምስራቅ ወለጋ ዞን በጊዳ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ በርካታ አማራዎች መገደላቸውና መፈናቀላቸው ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን በጊዳ ወረዳ ድሬ በተባለ ቀበሌ ከትናንት ህዳር 29 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ለሰዓታት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በአካባቢው ነዋሪ በሆኑ አማራዎችና በኦሮሚያ ልዩ ሀይል ላይ ተኩስ መክፈታቸው ተገልጧል። በዚህም እስካሁን በደረሰን መረጃ 7 አማራዎች የተገደሉ ሲሆን ከመካከላቸውም ሙላለም አዳነ፣ ባዬ እሸቱ እና ወርቅነሽ አባተ የተባሉ በጊዳ ወረዳ የድሬ ቀበሌ አማራዎች ስለመገደላቸው ነው የአይን እማኞች የተናገሩት። ድሬ ቀበሌ ላይ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና በኦነግ ሸኔ መካከል በተደረገው የተኩስ ለውውጥ ከሁለቱም ወገን በርካቶች ስለመጎዳታቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል። አሁን ላይ ልዩ ሀይሉ ከአቅማችን በላይ ነው በማለቱ ኦነግ ሸኔዎች አማራውን እየለዩ ለማፈናቀል በማለም ተኩስ መክፈታቸውን የጠቆሙት ነዋሪዎች የመከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው ማቅናቱ ቢገለፅም እስካሁን ግን አለመድረሱ ተገልጧል። ከድሬ እና አካባቢው የሚፈናቀሉ ከ2 ሽህ በላይ አማራዎች በኪረሞ ወረዳ መርጋ ጅሬኛ በተባለ ቀበሌ እንደሚገኙ ተጠቁሟል። ከጥቃቱ ሸሽቶ በጫካ ከሚገኝ የአካባቢው ነዋሪ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply