በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ እና አካባቢው ታስረው የነበሩ አማራዎች ተፈተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል ጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኪረሞ ሀሮ አዲስ ዓለም እና…

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ እና አካባቢው ታስረው የነበሩ አማራዎች ተፈተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል ጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኪረሞ ሀሮ አዲስ ዓለም እና አካባቢው ያለማንም ተከላካይ እና እርዳታ ሰጭ በሽብር ቡድኑ ግልጽ ጦርነት የተከፈተበትን አማራ እየታደጉ የነበሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው አማራዎች ከጥቅምት 5 ቀን 2014 ጀምሮ መታሰራቸውን አሚማ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ መዘገቡ ይታወቃል። በመንግስት መዋቅር ሆነው የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን ፍላጎት እንዲሳካ እየተባበሩ ነው በተባሉ አካላት ታስረው ከቀናት የእስር ቆይታ ከተፈቱት መካከል:_ 1) አዲስ አላምረው፣ 2) ጅብሪል አባቡዬ 3) አስናቀው ካሳው፣ 4) መሀሙድ አሊ ይብዛ 5) አብዱ ኢብራሂም 6) ሽመልስ በድሩ 7) ሳለእግዜር እንዳለው አላምረው ጥቅምት 9 ቀን 2014 በሰው ዋስ መፈታታቸው ታውቋል። አቶ ንጉሴ ደባልቄ ደግሞ በጥቅምት 14 ቀን 2014 ተፈተዋል። በተመሳሳይ 8: መሀመድ አሊ ሀሰን እና 9) ሀሰን መሀመድ ደግሞ በዛሬው እለት ጥቅምት 16 ቀን 2014 ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ የሰው ዋስ በማስያዝ እንደተፈቱ ተገልጧል። በኦሮሚያ ክልል በተለይ ምስራቅ ወለጋ ዞን ባለሃብቶችና ተሰሚነት ያላቸው አማራዎች በተለያዩ ጊዜያት አላግባብ እየታሰሩ ነው በሚል ተደጋጋሚ ቅሬታዎች ይቀርብበታል። እንደአብነትም ከጊዳ አያና ወረዳ መንደር 10 ታፍነው ወደ ነቀምት ተወስደው የታሰሩት 31 የሚሆኑ የአማራ ባለሀብቶች ጉዳይ ተጠቃሽ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply