You are currently viewing በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ መከላከያ ሰራዊት መግባቱ ተሰምቷል፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ እስካሁን የደረሰባቸውን በደል ሁሉ ለመከላከያ ለመናገር ያቀኑ ሰዎች ክልከላ እንደተደረገባቸው ገልጸዋ…

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ መከላከያ ሰራዊት መግባቱ ተሰምቷል፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ እስካሁን የደረሰባቸውን በደል ሁሉ ለመከላከያ ለመናገር ያቀኑ ሰዎች ክልከላ እንደተደረገባቸው ገልጸዋ…

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ መከላከያ ሰራዊት መግባቱ ተሰምቷል፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ እስካሁን የደረሰባቸውን በደል ሁሉ ለመከላከያ ለመናገር ያቀኑ ሰዎች ክልከላ እንደተደረገባቸው ገልጸዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 1 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከሰሞኑ በምስራቅ ወለጋ ዞን መከላከያ ሰራዊት አያሌ ግፍ እና በደል ሲፈጸምበት ወደከረመው ኪረሞ ወረዳ ከብዙ ግድያ፣ መፈናቀል፣ ዝርፊያ፣ ጩኸትና ለቅሶ በኋላ መግባቱ ተሰምቷል። መከላከያ ከመግባቱ ስለደረሰባቸው ህልቆ መሳፍርት የሌለው ግፍ እና በደል ለማስረዳትና አቤቱታ ለማቅረብ ተሰልፈው የሄዱትን በርካታ አማራዎች ከመከላከያ ጋር እንዳይገናኙ መከልከላቸውን አስታውቀዋል። አቤቱታ አቅራቢዎች ከመከላከያ ጋር እንዳይገናኙ ክልከላ ያደረጉትም የኪረሞ ወረዳ የሚሊሻ ኃላፊ አቶ ወንዴ እና አቶ ሁንደራ የተባሉ የኪረሞ ወረዳ ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ ናቸው። ለመከላከያ አቀባበል ያደረጉ አማራዎችም ከሽብር ቡድኑ ጋር በሚገናኙ ካድሪዎች ዘንድ ጥርስ እየተነከሰባቸው መሆኑ ተገልጧል። ለምን እንዲህ ዓይነት አቀባበል አደረጉ በሚል ቁጭት ያደረባቸው የነፍሰ ገዳይ ተባባሪዎች በከንቲባ ቢሮ በዝግ ተሰብስበው ስለመዋላቸውና በምን ጉዳይ እንደተወያዩም ከተሳታፊ የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ስለሽብር ቡድኑ ለመከላከያ መረጃ አሳልፈው ይሰጣሉ የተባሉ አመራሮችም እንዲቀየሩ እየተደረገ ነው፤ ይህም መረጃ የማጥፋት አንደኛው መንገዳቸው ነው ይላሉ። ታህሳስ 26 ቀን 2014 በኪረሞ ወረዳ አሹ እና ሲኒዶሮ በተባሉ ቀበሌዎች የቀሩ የአማራዎችን ቤት እየዞሩ ሲያቃጥሉ ስለመዋላቸው የአሚማ ምንጮች ተናግረዋል። የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድኑ አባላት በጊዳ አያና ወረዳ ቆቆፌ በተባለ አካባቢ በብዛት በመኪና እየተራገፉና ወደ ወዴሳ ዲማ ቀበሌ እየተጠጉ በመሆናቸው ከፍተኛ ስጋት አለብን ብለዋል። አዲስ በገቡት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይም ከደጋፊ ካድሪዎች ጋር ተመሳጥረው እርምጃ እንዳይወስዱባቸው ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ብለዋል። በኪረሞ ወረዳ የሀሮ አዲስ ዓለምን ጨምሮ በሌሎች ቀበሌዎች ቢያንስ ከ50 ሽህ በላይ ተፈናቃይ አማራዎች መንገድ በሽብር ቡድኑ ለወራት በመዘጋቱና አቅርቦት ባለመኖሩ በከፍተኛ ችግር እየተንገላቱ ይገኛሉ። በኪረሞ ወረዳ በነሃሴ 12 ቀን 2013 ብቻ ከ300 በላይ አማራዎች መርጋ ጅሬኛ በተባለ ቀበሌ የተጨፈጨፉ መሆኑ ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply