“በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ መግደል እንጅ ማዳንን የማያውቀው ነፍሰ ገዳዩ የኦነግ ሸኔ ጽንፈኛ ቡድን ተደብቆ ጥቃት መፈፀምን መደበኛ ስራው አድርጓል” ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲ…

“በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ መግደል እንጅ ማዳንን የማያውቀው ነፍሰ ገዳዩ የኦነግ ሸኔ ጽንፈኛ ቡድን ተደብቆ ጥቃት መፈፀምን መደበኛ ስራው አድርጓል” ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲ…

“በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ መግደል እንጅ ማዳንን የማያውቀው ነፍሰ ገዳዩ የኦነግ ሸኔ ጽንፈኛ ቡድን ተደብቆ ጥቃት መፈፀምን መደበኛ ስራው አድርጓል” ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን በተለይ በኪረሞ እና አንገር ጉትን አካባቢዎች በፀረ አማራና ፀረ ኢትዮጵያ ትርክቱ የሚታወቀው የዘር አጥፊው የህወሀት ሌላኛው ክንፍ ኦነግ ሸኔ ማንነትንና ሀይማኖትን ቆጥሮ በንፁሀን አማራዎች ላይ አሰቃቂ ግድያ፣ማፈናቀልና ዝርፊያ መፈፀምን የመደበኛ ስራ ያህል ይዞ እንደሚንቀሳቀስ ነው ነዋሪዎች የገለፁት። “የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከመንግስት ጋር ስምምነት ያላቸው ይመስል እንደ አሸን እየፈሉ ነው” ያሉት ነዋሪዎች በተለያዩ አካባቢዎች ግዳይ እንደጣለ ጀግና በሰላም ሲንጎባለሉ ቢታዩም የሚነካቸው የለም ነው የተባለው። ጥቅምት 22 ቀን 2013 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ በጋዋ ቃንቃ ቀበሌ ላይ አስገድዶ እና አታሎ በሰበሰባቸው ንፁሀን የአማራ ተወላጆች ላይ በአሰቃቂ መልኩ የጅምላ ጭፍጨፋ የመፈፀማቸው አሳዛኝና አሳፋሪ የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚታወስ ነው። ይህን የጅምላ ጭፍጨፋ የፈፀመውና ጌታው ህወሀት የተነካበት ኦነግ ሸኔ ትናንት ጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓ.ም በምስራቅ ወለጋ ኪረሞ ወረዳ ባጊን ቀበሌ ላይ እንደለመደው በንፁሀን ላይ ተኩስ በመክፈት አንድ አቁስሏል ሲሉ ነው ነዋሪዎች የተናገሩት። በአማራ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየፈፀሙ ላሉት ለኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከማህበረሱ ውስጥ ስንቅና ትጥቅ የሚያቀብል፣ከኦህዴድ መዋቅርም መረጃ የሚያቀብል፣እከሌን በሉት፣መሳሪያውን ንጠቁት፣ ዝረፉት የሚል በወንጀሉ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ የሚሳተፍ እንዳለ ነው እየደረሱን ያሉ መረጃዎች ያመለከቱት። ነዋሪዎች ሲቀጥሉ በኦህዴድ ውስጥ ያሉ ጭምብል ለባሾች፣ በማስመሰልና በአድርባይነት የተጠመዱ አመራሮች ጭፍጨፋው ሲፈፀም ቀድመው ከቦታው በመሸሽ፣ጨለማ ስለነበር አልቻልንም በማለት፣ የሀይል እጥረት ስላጋጠመን፣ስልጠና ላይ ስለነበርን ነው፣ ሌላም በማለት ኦነግን በቃላት በማውገዝ በተግባር የማፅዳት ስራን እየሰሩ ነው ብለዋል። ትናንት ኪረሞ ወረዳ ባጊን ቀበሌ ላይ ከቀኑ 12 ሰዓት አካባቢ በከፈቱት ተኩስ ከኦነግ ሸኔ የቆሰለ ስለመኖሩና ለጊዜውም ቢሆን መሸሻቸው የተነገረ ሲሆን ማህበረሰቡ በየበሩ ሆኖ ራሱንና ቤተሰቦቹን ከአሸባሪው የኦነግ ሸኔ ቡድን ለመታደግ ጥረት እያደረገ መሆኑ ነው የተገለፀው። እነ አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሚመሩት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትም ሆነ እነ ጠ/ሚ አብይ አህመድ የሚመሩት መንግስት የመከላከያ ሰራዊትን ከአካባቢው በማስወጣት ስለምን ህዝብን ለነፍሰ ገዳዮች አስረክበው እንደሚሄዱ ግልፅ አይደለም ያሉት ነዋሪዎቹ እኛ እንድናልቅና እንድንፈናቀል ስምምነት አላቸው ብለን እንድናስብ እየተገደድን ነው ብለዋል። “የመከላከያ ሰራዊትን ከአካባቢው ማስወጣት ማለት ለኦነግ ነጻ የግደሉ ፍቃድ እንደመስጠት ነው!” ብለዋል የኪረሞ ነዋሪዎች።

Source: Link to the Post

Leave a Reply