በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ በሀሮ አዲስ ዓለም እና በወዴሳ ዲማ ተከፍቶ በዋለው መንግስት መር ጦርነት በርካታ አማራዎች በግፍ ተገድለዋል፤ ብዙዎች ቆስለዋል፤ ጭሆታቸውን ሰምቶ የደረሰላቸ…

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ በሀሮ አዲስ ዓለም እና በወዴሳ ዲማ ተከፍቶ በዋለው መንግስት መር ጦርነት በርካታ አማራዎች በግፍ ተገድለዋል፤ ብዙዎች ቆስለዋል፤ ጭሆታቸውን ሰምቶ የደረሰላቸው አካል እንደሌለም ተናግረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 16 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የኦሮሚያ ክልል መንግስት በዋናነት ስምሪት በመስጠት የላከው የክልሉ ልዩ ኃይል ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና ከሌሎች ተባባሪዎቹ ጋር በመተባበር በፈጸሙት በቡድን መሳሪያ የታገዘ ጥቃት በርካታ አማራዎች ተገድለዋል፤ ብዙዎች መቁሰላቸውም ተሰምቷል። በኪረሞ ወረዳ ከአንድ መቶ ሽህ በላይ ተፈናቃዮች በሚገኙበት ሀሮ አዲስ ዓለም ታህሳስ 14/2015 ከንጋት ጀምሮ በአማራ ላይ የተከፈተው ጦርነት ከሰዓት በኋላ በረድ ማለቱ ተገልጧል። ዳሩ ግን እስካሁን ጭሆታቸውን ሰምቶ የደረሰላቸው አካል የለም። አራት ጊዜ ወረራ በመፈጸም ከተቆጣጠራት ኪረሞ በመነሳት በአራት አቅጣጫ ነበር በሀሮ አዲስ ዓለም ላይ ወረራ የተፈጸመው። ብዙ ሽህ ሰዎች አሁንም ነፍሳቸውን ከጨካኞች ለማዳን ሲባል በየጫካው እየተንከራተቱ ነው። በተመሳሳይ በተለያዩ አቅጣጫዎች ወዴሳ ዲማ የተባለ የኪረሞ ቀበሌን ሲከብ የዋለው ይህ መንግስት መር ጥምር ጦር ከቀኑ 8 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት ድረስ ከፍተኛ ተኩስ በመክፈት ጉዳት ማስከተሉ ታውቋል። በወረራ እና በጭፍለቃ የተሰማሩ መንግስት መር የቡድን መሳሪያ የታጠቁ አካላት ኔት ወርክ እንዲዘጋ በመደረጉም ድምፅ አልባ ጭፍጨፋቸውን አጠናክረው እንዲፈጽሙ ሰፊ እድል አግኝተዋል። በኦሮሚያ ይህ ሁሉ ተደጋጋሚ እና የተደራጀ የዘር ፍጅት እየተፈጸመ መሆኑ እየታወቀ የሚያስቆመውም ሆነ ፍጅቱን የፈጸሙ እና በጥቃቱ የተሳተፉ አካላት ተጠያቂ ሲሆኑ አለመታዬቱ ብዙዎችን እያሳዘነ እና ከጊዜ ወደ ጊዜም ተስፋ እያስቆረጠ ያለ ጉዳይ ሆኗል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) የደረሰውን ጉዳት እያጣራ ለህዝብ የሚያደርስ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply