You are currently viewing በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ ተሰሚነት ያላቸውን አማራዎች እየታሰሩ መሆናቸው ተገለጸ፤ በዛሬው እለት ብቻ ሶስት አማራዎች ታስረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ…

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ ተሰሚነት ያላቸውን አማራዎች እየታሰሩ መሆናቸው ተገለጸ፤ በዛሬው እለት ብቻ ሶስት አማራዎች ታስረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ…

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ ተሰሚነት ያላቸውን አማራዎች እየታሰሩ መሆናቸው ተገለጸ፤ በዛሬው እለት ብቻ ሶስት አማራዎች ታስረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ ተሰሚነት ያላቸውን አማራዎች እየታሰሩ መሆናቸው ተገለጸ፤ በዛሬው እለት ብቻ ሶስት አማራዎችን ለአማራ ሚዲያ ማዕከል(አሚማ) ከስፍራው የደረሰው መረጃ አመልክቷል። ከአሸባሪቅ ኦነግ ሸኔ ጋር አብሮ እየሰራ ነው በሚል የሚወቀሰው የኪረሞ ወረዳ መስተዳድር አማራን ከጥቃት የሚታደጉ ጀግኖችን እያደነ እያሰረ መሆኑ ተነግሯል። እንደአብነትም በዛሬው እለት ጥቅምት 5 ቀን 2014 ለአማራው ይቆረቆራሉ፤ ይታገላሉ ከተባሉት መካከል:_ 1) አቶ ሙስጠፌ 2) አቶ አስናቀው እና 3) አቶ ሀሰን መሀመድ የተባሉ አማራዎች ታስረዋል። በሚሊሻነት ከሀሮ ተመልምለው ወደ ኪረሞ ከተወሰዱ በኋላ ንጉስ ደባልቀው ካሳው አቸነፈ ይብሬ ይመር፣ ጀምበሩ አበባው፣ ፈንታሁን አበዛው በወረዳው ከ19 ቀበሌዎች መካከል ሀሮ፣ጨፌ ጉዲና፣ ባጊንና ኪረሞ ብቻ በሽብር ቡድኑ አለመያዛቸው ተገልጧል። በተያያዘ የኪረሞ ወረዳ መስተዳድር ት/ቤት ገብቶ 30 የሚሆኑ ተማሪዎችን በመመልመል ጦር መሳሪያ ማስታጠቁ ተሰምቷል። በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች አማራው እንደ እናንተ ሰው ነውና ለምን ይጨፈጨፋል በሚል የሚጠይቁና የሚታገሉ አማራዎችን ከመግደል በተጨማሪ ማሰር የተለመደ ሆኗል። በምስራቅ ወለጋ ዞን ጉዳ አያና ወረዳ መንደር 10 ብቻ ከጥር 2013 ጀምሮ 31 የሚሆኑ የአማራ ባለሀብቶች ያለበደላቸው እና ያለጠያቂ ወደ ነቀምት ተወስደው በአስከፊ እስር ላይ እንደሚገኙ ተወስቷል። በአቢ ደንጎሮ ወረዳም ከተለያዩ ቀበሌዎች ተወስደው የታሰሩ በርካታ አማራዎች መኖራቸውን በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply