በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ ዋሊ ልጉማ አካባቢ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በሚፈፅሙት አማራ ተኮር ጥቃት የቆሰለ ስለመኖሩና በርካቶች ስለመፈናቀላቸው ነዋሪዎች ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ ዋሊ ልጉማ አካባቢ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በሚፈፅሙት አማራ ተኮር ጥቃት የቆሰለ ስለመኖሩና በርካቶች ስለመፈናቀላቸው ነዋሪዎች ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ ዋሊ ልጉማ አካባቢ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በሚፈፅሙት አማራ ተኮር ጥቃት የቆሰለ ስለመኖሩና በርካቶች ስለመፈናቀላቸው ነዋሪዎች ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን በኪረሞ ወረዳ በዋሊ ልጉማ ቀበሌ ትናንት ጥቅምት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት 2 ሰዓት ላይ በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ የአማራ አርሶ አደሮችን ጦር መሳሪያ ለመንጠቅና ለመጨፍጨፍ ተኩስ ከፍተው ማምሸታቸው ተገልጧል። ይህን ተከትሎም አንድ የአማራ አርሶ አደር ቆስሎ ወደ አማራ ክልል ለህክምና እርዳታ መወሰዱንና ከ200 ያላነሱ አማራዎች በአባይ አፋፍ አካባቢ ከዋሊ ልጉማ ቀበሌ ለቀው ወደ ኪረሞ ወረዳ አዋሳኝ ወፍቲ ቀበሌ ከዘመድ የተጠጉ መሆኑን ተፈናቃዮች ጠቁመዋል። እንደተፈናቃዮች አገላለጽ ከአካባቢው የኦሮሞ ተወላጆች መካከል በርካቶች ለኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች አድረው ትጥቅና ስንቅ እያቀበሉ ስለመሆኑ እንዲሁም የኦሮሚያ ልዩ ሀይልም ኦነጎችን ለማጥቃት እንደማይጨክንባቸው ተናግረዋል። የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በኪረሞ ወረዳ ደኔቮ በተባለ ጎራ የተለያዩ ከባድ መሳሪያዎችን ለ3 እና ለ4 በመሆን ሲወስዱ እንደሚታዩም ህዝቡም ሆነ የፀጥታ አካሉ ያውቃል ብለዋል። በኪረሞ ወረዳ ዋሊ ልጉማ ቀበሌ በአማራ አርሶ አደሮች ላይ ትናንት ምሽት ከተከፈተው ተኩስ ጋር ተያይዞም የተገደለ ሊኖር እንደሚችልም ጠቁመዋል። በበርካታ የኦሮሞ ተወላጆች ዘንድ መንግስት ያስታጠቃቸውን መሳሪያ ለኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ያለምንም መከላከል የማስረከብ ሁኔታ እየተለመደ መምጣቱን የገለፁት ምንጮች በእጅ አዙር መንግስት ለኦነግ ጭምር እያስታጠቀ ይመስላል ብለዋል። አማራው ጥይት ካልጨረሰና ካልተመታ በስተቀር የጦር መሳሪያውን ለኦነግ አሳልፎ አይሰጥም ያሉት ነዋሪዎች መሳሪያ ቢኖረውም ባይኖረውም ህጻን ትልቅ ሳይለዩ ሲገድሉትና ሲያፈናቅሉት ይስተዋላልም ብለዋል። በመሆኑም የሚመለከተው የመንግስት አካል በአካባቢው የመከላከያ ሰራዊትን በማሰማራት የህዝቡን ሰላምና ደህንነት እንዲያስከብር፣ ዓመቱን ሁሉ የለፋንበትን አዝመራ እንድንሰበስብ በማድረግ ረገድ እንዲተባበረን ነው የምንጠይቀው ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply