You are currently viewing በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ 9 ቤተሰቦቻቸውን በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በእኩይ አላማ ተጋሪዎቹ በግፍ የተጨፈጨፉባቸው አባት የእርዳታ ጥሪ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   የካቲት…

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ 9 ቤተሰቦቻቸውን በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በእኩይ አላማ ተጋሪዎቹ በግፍ የተጨፈጨፉባቸው አባት የእርዳታ ጥሪ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት…

በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ 9 ቤተሰቦቻቸውን በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በእኩይ አላማ ተጋሪዎቹ በግፍ የተጨፈጨፉባቸው አባት የእርዳታ ጥሪ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 18 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ 9 ቤተሰቦቻቸውን በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በእኩይ አላማ ተጋሪዎቹ ነሃሴ 29 ቀን 2013 እና መስከረም 3/2014 በግፍ የተጨፈጨፉባቸው አባት የእርዳታ ጥሪ አቅርበዋል። አምስት ልጃቸውን የያዙ ባለቤታቸው ከጥቃት ሸሽተው ወደ ምድረገኝ ከሚሴ የተሰደዱ ቢሆንም ከተጠጉበት አካባቢም በአሸባሪው ትሕነግ እና ኦነግ ሸኔ በተፈጸመው ወረራ ዳግም ተፈናቅለው ወደ ሰሜን ሸዋ ዞን ማጀቴ መጓዛቸው ተገልጧል። ባለቤታቸው አቶ ቸሩ ደግሞ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና የእኩይ አላማ ተጋሪዎቹ መንገድ በመዝጋታቸው በአፈና ላይ ካሉት ብዙ ሽህ የኪረሞ እና የሀሮ አዲስ ዓለም አማራዎች መካከል አንዱ ናቸው። አቶ ቸሩ ስለሀገር እና ስለወገን ተብሎ ስለሚደረግ ትግል አውርተው አይጠግቡም። ከ1990 ጀምሮ እስከ 1998 ዓ/ም በባድመ፣በጾሮና እና በዛላንበሳ ሁሉ በመታገል እስከ 8 ዓመት ድረስ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ አገልግለዋል። ከ8 ዓመት የትግል ቆይታ በኋላ በክብር ተሰናብተው ወደ ኪረሞ በመምጣት የጥበቃ ሰራተኛ በመሆን ለ3 ዓመት አገልግለዋል። ኪረሞ ወረዳ በቀናት ልዩነት 9 ቤተሰቦቻቸውን የተነጠቁት እኒህ አባት ክፉኛ መቸገራቸውን በመግለጽ የወገንን እርዳታ ጠይቀዋል። አቶ ቸሩ ፈንታሁን በግፍ የተገደሉባቸው የልጅ፣ የአባት እና የእናት ስም:_ 1) ፈንታሁን ታከሉ፣ እድሜያቸው 80 ዓመት፣ 2) ወ/ሮ ቀበነች ሙለታ፣ እድሜያቸው 70 ዓመት አቶ ፈንታሁን እና ወ/ሮ ቀበነች መስከረም 3/2014 ለቅሶ ላይ በተቀመጡበት ቤት ከምሽቱ 3 ሰዓት በጥይት የተገደሉ ናቸው። በተመሳሳይ ነሃሴ 19/2013 በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በዘር ማጥፋት ተባባሪዎቹ በግፍ የተገደሉትም:_ 3) መለሰ ቸሩ_ትልቅ ልጃቸው። በትምህርቱ 8ኛ ክፍል ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረ። 4) ወ/ሮ ሙሌ ፈንታሁን፣ (የአቶ ቸሩ ትልቅ እህት) ቸሩ ፈንታሁን ከመከላከያ እንደተመለሱ በወ/ሮ ሙሌ ቤት ተጠግተው እገዛ ሲደርግላቸው ነበር። 5) ሽብሩ መንጋው፣(12ኛ ክፍል የደረሰ) 6) አሰፉ መንጋው፣11ኛ ክፍል፣ 7) ማሪቱ መንጋው፣7ኛ ክፍል፣ 😎 ፍቅር አዲስ መንጋው፣የ3 ዓመት ህጻን ልጅ። 9) አበራ ፍቃዱ_የኦሮሚያ ባንክ ሰራተኛ ነበር። (የወንድማቸው ልጅ) ሁሉም በአማራዊ ማንነታቸው በግፍ ተገድለዋል። አበራ ፍቃዱ ነሃሴ 29/2013 ወደ ለቅሶ ሲሄድ መንገድ ላይ በቆዩ የኦነግ አባላት የተገደለ ነው። አባቱ ቀደም ብሎ በህመም ህይወቱ አልፏል። ይባስ ብሎ ከበደል ላይ በደል ከጥር 2/2014 እስከ የካቲት 11/2014 ሌላ ነገር ያስባሉ በሚል ለ40 ቀን ታስረው እንደነበርም ገልጸዋል። የባለቤታቸው ስምም ወ/ሮ የውብዳር መንገሻ ሲሆኑ የተረፉ 5 ልጆችን ይዘው ከሚሴ እንደነበሩ፣ በመቀጠልም ባለቤታቸው በህወሓትና በኦነግ ሸኔ ጥምር ወረራ ወቅት ከእነ ልጆቻቸው ዳግም ተባረው አሁን ላይ ኑሯቸውን በሰሜን ሸዋ ዞን ማጀቴ ማድረጋቸው ተገልጧል። መርዳት ለምትፈልጉ:_ ቸሩ ፈንታሁን ታከሉ፣ ስልክ 0968364658 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 10000458303208 ለተጨማሪ መረጃ:_ ወ/ሮ የውብዳር መንገሻ (የአቶ ቸሩ ባለቤት) ስልክ_ 0920184910 በመጠቀም መደወል ይችላሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply