You are currently viewing በምስራቅ ወለጋ ዞን ዋዩጡቃ ወረዳ የቡኒያ ሙሉ ቀበሌ አማራዎች ሱቅ፣ ቤትና ሙሉ ሀብታቸው በኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድንና በተባባሪዎቹ በእሳት እየወደመ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ጥቅምት…

በምስራቅ ወለጋ ዞን ዋዩጡቃ ወረዳ የቡኒያ ሙሉ ቀበሌ አማራዎች ሱቅ፣ ቤትና ሙሉ ሀብታቸው በኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድንና በተባባሪዎቹ በእሳት እየወደመ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት…

በምስራቅ ወለጋ ዞን ዋዩጡቃ ወረዳ የቡኒያ ሙሉ ቀበሌ አማራዎች ሱቅ፣ ቤትና ሙሉ ሀብታቸው በኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድንና በተባባሪዎቹ በእሳት እየወደመ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 18 ቀን 2014 ዓ. ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ዋዩጡቃ ወረዳ የቡኒያ ሙሉ ቀበሌ አማራዎች ሱቅ፣ ቤትና ሙሉ ሀብታቸው በኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድንና በተባባሪዎቹ በእሳት እየወደመ መሆኑን ነዋሪዎች ለአሚማ ተናግረዋል። ጥቅምት 17 ቀን 2014 ከመኮፋ እና ከጣጢስ የተፈናቀሉ በሽህ የሚቆጠሩ አማራዎች የድረሱልን ጥሪ ማሰማታቸው ይታወቃል። በተለይ ከጥቅምት 15 ቀን 2014 ጀምሮ የሽብር ቡድኑ ተኩስ መክፈቱነ ተከትሎ ህዝቡ ለቆ ወደ ወረዳው ዋና ከተማ ጉቴ መሰደዱ ይታወቃል። በትናንትናው እለት ጣጢሳ በሚባለው የገጠር መንደር ያለ መስጊድን ለማቃጠል ሙከራ ተደርጎ በሚሊሾች መክሸፉ ተነግሯል፤ በርካታ ቤቶችም ተቃጥለዋል። በዛሬው እለት ጥቅምት 18 ቀን 2014 ከቀኑ ከጠዋቱ ጀምሮ አውዳሚ ቡድኑ የአማራዎችን ቤት እያቃጠለ መሆኑ ተረጋግጧል። ሱቆች፣ሆቴሎችና መኖሪያ ቤቶች እየወደሙ ነው። በአካባቢው ያሉ ውስን የአማራ ሚሊሾች ለመከላከል ጥረት እያደረጉ ቢሆንም ከአቅም በላይ መሆኑ ተገልጧል። የዋዩጡቃ ወረዳ አስተዳዳሪ የተፈናቀለ የለም፤ ኃይልም አሰማርተናል ሲሉ ማስተባበላቸው ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply