በምስራቅ ወለጋ ዞን የስቡ ስሬ ወረዳ ነዋሪዎች ኦነግ ሸኔን አወገዙ

በምስራቅ ወለጋ ዞን የስቡ ስሬ ወረዳ ነዋሪዎች ኦነግ ሸኔን አወገዙ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን የስቡ ስሬ ወረዳ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ኦነግ ሸኔን አውግዘዋል፡፡
ሰልፈኞቹ “ኦነግ ሸኔ አፋን ኦሮሞ የሚናገር ወያኔ ነው”፤ “በኦነግ ሸኔና በወያኔ መቃብር ላይ ብልጽግናን እናረጋግጣለን” የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል፡፡
የስቡ ስሬ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ተመስገን ገመዳ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ኦነግ ሸኔ በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለው ተግባር አሳፋሪ ነው ብለዋል፡፡
እንደ ኦቢኤን ዘገባ የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዓለማየሁ ተስፋ በበኩላቸው÷ ኦነግ ሸኔ ዓላማና ግብ የሌለው፣ የጽንፈኛው ህወሃት ቡድንን እቅድ ለማሳካት የሚሰራ ቡድን ነው ብለዋል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በምስራቅ ወለጋ ዞን የስቡ ስሬ ወረዳ ነዋሪዎች ኦነግ ሸኔን አወገዙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply