በምስራቅ ወለጋ ዞን የአንገር ጉትን ነዋሪዎች ስርዓቱ የአካባቢውን ወቅታዊ ሁኔታ በመከታተል ህዝቡን የሚታደግ እና መንግስትነቱንም የሚመጥን ስራ እንዲሰራ ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መ…

በምስራቅ ወለጋ ዞን የአንገር ጉትን ነዋሪዎች ስርዓቱ የአካባቢውን ወቅታዊ ሁኔታ በመከታተል ህዝቡን የሚታደግ እና መንግስትነቱንም የሚመጥን ስራ እንዲሰራ ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መ…

በምስራቅ ወለጋ ዞን የአንገር ጉትን ነዋሪዎች ስርዓቱ የአካባቢውን ወቅታዊ ሁኔታ በመከታተል ህዝቡን የሚታደግ እና መንግስትነቱንም የሚመጥን ስራ እንዲሰራ ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 15 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አካባቢያችን ከቀን ወደ ቀን በፀረ አማራ እና ፀረ ኢትዮጵያ የሽብር ኃይሎች እየተከበበ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ እየደረሰን በመሆኑ ስጋት አለን ብለዋል በምስራቅ ወለጋ ዞን የአንገር ጉትን ከተማ ነዋሪዎች። መንግስትም ከማህበረሰቡ የሚደርሱትን ጥቆማዎችን ትርጉም እየሰጠ ህዝቡን እየታደገ እንዳልሆነ የሚገልፁት ነዋሪዎች አሁንም በአካባቢው በቂ ኃይል መድቦ በንፁሃን ላይ ሊፈፀም ከሚችል ጥቃት መታደግ አለበት ብለዋል። ስርዓቱ መንግስትነቱን የሚመጥን የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የማስከበር ስራ እንዲሰራ የጠየቁት ነዋሪዎቹ ጊዳ አያና ፣አቢደንጎሮና ጃርዴጋ ጃርቴ ወረዳዎች የተፈፀመው እልቂት በራሱ ችግር በመሆኑ ከቶም ከተጠያቂነት አያመልጥም ብለዋል። አሁንም ቀድመን የምንናገረው በአማራ ላይ ከዚህ በላይ ተጨማሪ ጥቃት እንዳይፈፀም የሚመለከተው የመንግስት አካልና የወገኔ ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሁሉ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ለማሳሰብ ጭምር ነው ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply