በምስራቅ ወለጋ ዞን የኪረሙ ወረዳ መቀመጫ በሆነችው ኪረሙ ከተማ ኦነግ ሸኔ ከትናንት ጀምሮ በአማራ ተወላጆች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት እያደረሰ እንደሚገኝ ነዋሪዎች ተናገሩ! ሕዳር 10 ቀን 20…

በምስራቅ ወለጋ ዞን የኪረሙ ወረዳ መቀመጫ በሆነችው ኪረሙ ከተማ ኦነግ ሸኔ ከትናንት ጀምሮ በአማራ ተወላጆች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት እያደረሰ እንደሚገኝ ነዋሪዎች ተናገሩ! ሕዳር 10 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ትናንት ጀምሮ በቀጠለው የአማራ ተወላጆችን ኢላማ ባደረገው ጥቃት በርካቶች መሞታቸውን ነዋሪዎች ለአሻራ በስልክ ገልፀዋል። ከመንግስት ድጋፍ የሚደረግለት ኦነግ ሸኔ የኪረሙ ወረዳ አስተዳደር አቶ ፍቃዱ ጉዳዩን ወደተባባሰ ደረጃ ለማድረስ ከክልሉ የጸጥታ ቢሮ ጋር በመደዋወል ከፍተኛ ቁጥር ያለው የክልሉን ልዩ ሐይል ወደ ቦታ እንዲያቀና በትናንትናው እለት እ ጥሪ አቅርበዋል ሲሉ ነዋሪዎች ለአሻራ ገልፀዋል ። በዚህም የተነሳ የመጣው የክልሉ ልዩ ሐይል በጉትን ከተማ መዘጋጃ ቤት ካደረ በኋላ በአሁኑ ሰዓት ከባድ መሳሪያዎችን በመያዝ ወደኪረሙ ወረዳ እየገባ ይገኛል። ጉዳዩ በፌዴራል መንግስት ሐይሎች እንዲታይ ጥረት ቢደረግም የመከላከያ ሐይል ግን እስካሁን ለመግባት አልቻለም ብለዋል። በኪረሙ ወረዳ እየተመመ የገባው ሐይል በወለጋ ለሚገኙት የአማራ ማህበረሰብ ከፍተኛ ስጋትን በመፍጠሩ ሁሉም ስጋት ላይ ይገኛል። በዚህ ውጥረት ውስጥ የኪረሙ ማህበረሰብ በሙሉ፦ ** የአንዶዴ ** የአሊ ** የጫንጮ ** የቱሉጋና ** የሐሮ አድስ አለም ** የጉትን ** የመዳሎ ** የአጋምሳ ** የጃርቴ ** የጃርዴጋ እና ** የለገሐድ አከባቢ ማህበረሰብ ወገኖች በመሆናቸው ሁሉም የጉዳዩን በጥልቀት ተመልክቶ የፌዴራል መንግስት በአስቸኳይ ውጥረቱ የሚረግብበትን አማራጭ እንዲሰጠው እየተጠባበቀ ይገኛል ተብሏል ። በኪረሙ ወረዳ ስር የምትገኘው የሐሮ አዲስ አለምና የአንዶዴ፣ አሊ አሁን ውጥረት ላይ እንደሆነች እየተነገረ ነው ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply