በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ በ01 ቀበሌ መንደር 10 በሚኖሩ አማራዎች ላይ የኦሮሚያ የልዩ ኃይል አባላት የበለጠ ጉዳት እንዳያደርሱ መንግስት አስቸኳ

በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ በ01 ቀበሌ መንደር 10 በሚኖሩ አማራዎች ላይ የኦሮሚያ የልዩ ኃይል አባላት የበለጠ ጉዳት እንዳያደርሱ መንግስት አስቸኳይ ከአካባቢው የማስወጣትና የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ተጠየቀ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ሚያዝያ 5 ቀን 2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ

በገለልተኝነቱ ላይ በርካታ ቅሬታዎች እየተነሱበት ያለው በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ የሰፈረው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል የካቲት 2013 ከፈፀመው ጥቃት በተጨማሪ ዛሬ ሚያዝያ 5 ቀን 2013 እህላችን አናዘርፍም ባሉ አማራዎች ላይ ተኩስ ከፍቶ ውሏል።

በዚህም የተጎዳ ሰው መኖሩ ቢነገርም አሚማ በተኩሱ ምክንያት ብዙዎች ራሳቸውን ለማዳን ወደ ጫካ በመሸሻቸው እስካሁን የተገደሉ እና የቆሰሉ ስለተባለው በቂ መረጃ ማግኘት አልቻለም።

4 የአማራ ወጣቶችን አላግባብ በት/ቤት አስሯል የተባለው እና ከተደራጁ የኦሮሚያ ወጣቶች ጋር የአማራውን እህል እያዘረፈና እየዘረፈ ነው የሚል ቅሬታ የተነሳበት በአካባቢው የሰፈረው ልዩ ኃይል በገበሬዎች ላይ የከፈተው ተኩስ ማምሻውን ጋብ ማለቱ ተሰምቷል።

በጣት የሚቆጠሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ባንዴራ ይዘው በመግባት ልዩ ኃይሉ በቡድን መሳሪያ በመታገዝ የሚፈፅመውን ጥቃት በማስቆም መንደር 9 ላይ ነዋሪዎችን ሰብስበው ማወያየታቸው ተነግሯል።

ተኩሱ ለጊዜው የቆመ ቢሆንም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የክልሉ ልዩ ኃይል በአይሱዙ እና በፓትሮል ከነቀምትና ከጉትን በኩል የገባ መሆኑን የገለፁት ነዋሪዎች አሁንም ሌሊት ላይ ሌላ ተጨማሪ ግድያ እንዳይደርስብን መንግስት አስቸኳይ የመፍትሄ እርምጃ እንዲወስድ ተማፅነዋል።

ችግሩ ያለው መንደር 10 እና ችግር ፈጣሪውም ራሱ ልዩ ኃይሉ ሆኖ እያለ ልዩ ኃይሉን መንደር 10 አስፍረው መከላከያ ሰራዊትን በሰላም ወረዳ ኡኬ ቀርሳ ማስፈሩ የግድያ ፍቃድ እንደመስጠት በመሆኑ ተገቢ አይደለም ብለዋል።

“የገቡት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ኡኬ ቀርሳ ተመልሰዋል፤ በልዩ ኃይሉ ብቻ ነው የተከበብ ነው” የሚል ቅሬታ የቀረበ ቢሆንም አሚማ ተጨባጩን መረጃ ለማግኘት አልቻለም።

አሚማ ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘ የሚመለስ ይሆናል።


Source:- አማራ ሚዲያ ማዕከል

Source: Link to the Post

Leave a Reply