በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ ወረዳ ድሬ እና ቦቆ በተባሉ አካባቢዎች ኦነግ ሸኔዎችና ተባባሪ ቄሮዎች ህዳር 29 እና 30  በአማራዎች ላይ በፈፀሙት ዘር ተኮር ጥቃት በርካቶች ስለመገደላቸው፣ መቁ…

በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ ወረዳ ድሬ እና ቦቆ በተባሉ አካባቢዎች ኦነግ ሸኔዎችና ተባባሪ ቄሮዎች ህዳር 29 እና 30 በአማራዎች ላይ በፈፀሙት ዘር ተኮር ጥቃት በርካቶች ስለመገደላቸው፣ መቁ…

በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ ወረዳ ድሬ እና ቦቆ በተባሉ አካባቢዎች ኦነግ ሸኔዎችና ተባባሪ ቄሮዎች ህዳር 29 እና 30 በአማራዎች ላይ በፈፀሙት ዘር ተኮር ጥቃት በርካቶች ስለመገደላቸው፣ መቁሰላቸው፣መታገታቸውና በመቶዎች የሚቆጠሩ መፈናቀላቸው ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን በጊዳ ወረዳ ህዳር 29 ቀን 2013 ዓ.ም የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እና ተባባሪ ቄሮዎች በጋራ በመሆን በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይል ላይ ተኩስ መክፈታቸውንና ጉዳትም ስለማድረሳቸው መዘገባችን ይታወሳል። በዚህም ነዋሪዎች እንደገለፁት በጊዳ ወረዳ በድሬ ቀበሌ 7፣ በቦቆ ጎጥ 9 በድምሩ ከ16 በላይ አማራዎች የተገደሉ ስለመሆኑ ሰምቻለሁ ያሉት ምንጫችን የሺ ካሴ የተባለችን ሴት ጨምሮ ሌሎች ሴቶችም ታግተዋል። ላለፉት 3 ቀናት ከ4 ቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን በጫካ የሰነበቱት ተፈናቃይ በሰጡት ምስክርነት በጥቃቱ ተፈናቅለው ወደ ኪረሞ ወረዳ መርጋ ጅሬኛ ቀበሌ ያቀኑትንም ከ6 መኪና ሙሉ አማራዎችን አስገድደው እየመለሷቸው መሆኑን ተናግረዋል። የሚመለሱትም ለተጨማሪ ጥቃት ተጋላጭ ላለመሆናቸው አንዳችም ዋስትና የላቸውም ብለዋል። በማናውቀው ነገር ድንገት ተኩስ ተከፈተ፣ በርካታ አማራዎችና የኦሮሚያ ልዩ ሀይሎችም ተገደሉ ያለው ምንጫችን የተፈናቀለው አማራም ህይወቱን ለማትረፍ ወደ አጎራባች ወረዳ ኪረሞ መርጋ ጅሬኛ ቀበሌ ካቀናንበት በአመራር ቦታ ያሉ እንደ አቶ አላምረው ረታ አይነት መሀል ከተማና በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ የኦነግ ሰዎች በግዳጅ መልሰውናል ብለዋል። ተፈናቃዮች ተመልሰው የማይሄዱ ከሆነ እንጀራ አትስጧቸው በማለት ስለመከልከላቸው፤ አፈና ስለማድረጋቸውና በመጨረሻም እስከ 6 መኪና ሙሉ የሚደርስ አማራ በግዴታ ትናንትና ዛሬ ተጭኖ ወደ ጊዳ ወረዳ እንዲመለስ መደረጉንና ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ስለመኖሩ አስታውቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply