
በምስራቅ ወለጋ ዞን ጎብሰዮ ወረዳ በአኖ እና ባፈኖ አካባቢዎች ጥር 25 በአሸባሪ እና ወራሪ ኦነጋዊያን የተገደሉት አማራዎች ቁጥር ከ70 በላይ እንደሚሆን ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 30 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጎብሰዮ ወረዳ በአኖ እና ባፈኖ አካባቢዎች ከ70 በላይ አማራዎች በአሸባሪ እና ወራሪ ኦነጋዊያን መገደላቸውን ነዋሪዎች አረጋግጠዋል። በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ከተለያዩ የጎብሰዮ ወረዳ ቀበሌዎች እና ከአጎራባች ወረዳዎች በተለያዩ ጊዜያት በተደራጁ እና በታጠቁ ኦነጋዊያን በተፈጸመባቸው ማንነት ተኮር ጥቃት ተፈናቅለው በአኖ ከተማ የገቡ እና በከተማዋ እየኖሩ ያሉ አማራዎች የጥር 25/2015 ጥቃት ሰለባ መሆናቸውን መዘገቡ ይታወሳል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) እንዳጣራው በግፍ ከተገደሉት መካከል:_ 1) ኢብራሂም ሰይድ፣ 2) ሰይድ ሙላት፣ 3) ጋሻው ክብረት፣ 4) አብዱ ሰይድ፣ 5) አማን ሰይድ፣ 6) ሰለሞን በላይ፣ 7) መርዙቅ፣ 8 መሀመድ ይብሬ፣ 9) አብዱ ሱፊያን፣ 10) ደግነት፣ 11) ብርሃኑ፣ 12) ማሙላ፣ 13) ሸህ ሰይድ ሁሴን 14) ከማል መሀመድ፣ 15) ደምሴ ምስጋናው፣ 16) መሐመድ ቃሲም፣ 17) ካሳዬ ገዛሐኝ፣ 18) መሐመድ አደም፣ 19) ማርዬ እንድሪስ፣ 20) ኢብራሒም ሰይድ፣ 21) እማዋይ ይመር ከነ ባለቤቷ፣ 22) መሐመድ እስማኤል፣ 23) አሊ ሲራጅ፣ 24) መሐመድ ሸኪ፣ 25) የኑስ ሰይድ፣ 26) ሱፊያን ሰይድ፣ 27) ሁሴን አበባው፣ 28) ሰለሞን በላይ፣ 29) ታዴ አብደላ፣ 30) አለባቸው የሱፍ፣ 31) ሰይድ ሁሴን፣ 32) ወ/ሮ ረሂማ ታደገ፣ 33) ማርዬ፣ ከዚህ በተጨማሪም ከሚገደሉ አማራዎች ጎን ተሰልፋችኋል የተባሉ የሚከተሉት ሁለት የኦሮሞ ተወላጆችም ተገድለዋል። 1) ኦቦ መረራ፣ ንብረት ዝረፉ እንጅ የሰው ህይወት ለምን ታጠፋላችሁ” በማለታቸው የተገደሉ አባት ናቸው። 2) ጉተቻ ዘንገባ የተባለ አንድ የኦሮሞ ተወላጅ ምንድን ነው ብሎ ከቤቱ ሲወጣ የተገደለ ነው። የኦሮሚያ ክልል የመንግስት አካላት የአማራን ዘር ለማጥፋት ስንቅ፣ትጥቅ እና መረጃ በመስጠት እጀታ አድርገው የሚጠቀሙበት አሸባሪው የኦነጋዊያን ስብስብ የወረራ እና አሳዛኝ የጭፍጨፋ ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሎበታል። አብዛኞች ከጥቃቱ የተረፉ አማራዎች በየቀኑ ለትራንስፖርት እስከ 700 ብር እየከፈሉ ወደ አዲስ አበባ እየሸሹ መሆኑ ታውቋል።
Source: Link to the Post