
በምስራቅ ወለጋ ዞን ጎብሰዮ ወረዳ አኖ እና ባፈኖ አሳዛኝ ጭፍጨፋ መፈጸሙን ገለጸ። ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ እናት ፓርቲ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጎብሰዮ አካባቢ ስለተፈጸመው አማራ ተኮር ጭፍጨፋ የሚከተለውን አጋርቷል:_ ሀገር እንዲህ እየታመሰች ባላችበት ወቅትና የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ላይ በተፈጸመው ሕገወጥ ድርጊት ኹሉም ትኩረቱን ወደዚያ ባደረገበት አሳቻ ጊዜ ተጠብቆ ምሥራቅ ወለጋ ዞን ጎቡ ሰዮ ወረዳ አኖ ከተማ ላይ እንዲሁም መቂ እና ባፈኖ በሚባሉ አካባቢዎች “የኦነግ ሸኔ ቡድን” በቡድን መሣሪያና ስለት በመጠቀም ቤት ለቤት ሕዝብን እየጨፈጨፈ እንደሆነ ለፓርቲያችን የድረሱልን ጥሪ ያሰሙ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ሐሙስ ጥር 25 ቀን ንጋት 11:00 የጀመረው ጭፍጨፋ እስከ ምሽት መቀጠሉን፣ ከጭፍጨፋው የተረፉት ነዋሪዎችም የሞቱ ቤተሰቦቻቸውን አስከሬን እንኳን መሰብሰብ እንዳልቻሉ ገልጸዋል፤ የድረሱልን ጥሪም እያሰሙ ይገኛሉ። “የአማራ ማንነት ያላቸውን ነዋሪዎች እየመረጡ ለእናንተ ጥይት አናባክንም እያሉ በአሰቃቂ ኹኔታ ነው እየጨፈጨፉን ያሉት የሚሉት እማኞች ቤትና ሱቅ ሌላም ንብረት እየተመረጠ በጋሪ ጭምር ነው የተጫነው፣ ከተማዋን በአንድ ቀን ጠፍ ምድር አድርገዋታል” ብለዋል። በተጨማሪም “የተሻለ ይከላከልልናል የምንለው መከላከያ ነቀምት ላይ አለ ተባልን እስከ አኹን ግን አልደረሰለንም” ያሉት እማኞች “እንዲህ ከሰውነት በወጣ አኳኋን ስንጨፈጨፍ ደራሽ እንዴት ጠፋ? እኛ ሰው አይደለንም ወይ? ለምንስ እንድንጠፋ ተፈረደብን?” ሲሉ ጠይቀዋል። ፓርቲያችን ጉዳዩን እንደኹልጊዜው በቅርበት እየተከታተለው ሲሆን መከላከያ የእነዚህን ከጭፍጨፋው የተረፉና በማንነታቸው ምክንያት ያለማቋረጥ እንደዱር አውሬ እየተሳደዱ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቹን እንዲታደግ ተማጽኗችንን ለማቅረብ እንወዳለን። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post