በምስራቅ ወለጋ የሚኖሩ ንጹሀን አማራዎች ወደ አጎራባች ከተሞች እየተሰደዱ መሆኑ ተሰማ፡፡                አሻራ ሚዲያ        ታህሳስ፡-17/0…

በምስራቅ ወለጋ የሚኖሩ ንጹሀን አማራዎች ወደ አጎራባች ከተሞች እየተሰደዱ መሆኑ ተሰማ፡፡ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ፡-17/0…

በምስራቅ ወለጋ የሚኖሩ ንጹሀን አማራዎች ወደ አጎራባች ከተሞች እየተሰደዱ መሆኑ ተሰማ፡፡ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ፡-17/04/13/ዓ.ም ባህር ዳር በሁለት ቀን ውስጥ የአማራ ልጆችን ከምስራቅ ወለጋ ጨፍጭፈን እናጠፋለን የሚለውን አዋጅ ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን የአማራ ልጆች ወደ ተለያዩ አጎራባች ከተሞች እየተሰደዱ መሆኑ ተገልጻል። በምስራቅ ወለጋ ሊሙ ወረዳ አርቁምቢ ቀበሌ የአማራ ልጆችን በሁለት ቀን ውስጥ ስለምናጠፋ አማራ የሆናችሁ አከባቢውን ለቃችሁ ውጡ የሚለውን አዋጅ ተከትሎ ከአርቁምቢ መንደር 3 እና ከዋጃ የሚባሉ አከባቢዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን የአማራ ልጆች አከባቢውን ጥለው በመሰደድ ላይ ናቸው። አዋጁ ከተሰማ ወዲህ ምንም አይነት የጸጥታ አስከባሪ ወደ አከባቢው ባለመድረሱና ታጣቂዎቹ ጥቃት ማድረስ በመጀመራቸው ንጹሃን እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኖል ነው የተባለው። እንደምንጫችን ገለጻ መንግስት በንጹሀን ላይ የሚፈጸመውን ግፍ ማስቆም ባለመቻሉ ብዙ እንግልትና ሰቆቃ ደርሶብናል ብለዋል፡፡ ይህ የሚያሳየው ደግሞ ድርጊቱ መንግስታዊ መዋቅር መሆኑን ነው ብለዋል የችግሩ ሰለባዎች፡፡ አያይዘውም በንጸሀን አማራዎች ላይ የሚካሄደው የዘር ማጥፋት ወንጀል እስካሁን መቆም ያልቻለው የክልሉ መንግስትና የክልሉ ልዩ ሀይል ትዕዛዝ ሰጭና ተባባሪ ስለሆኑ ነው ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ይህን በንጹሃን የአማራ ልጆች ላይ እየተፈጸመ የሚገኘውን አሳዛኝ ግፍ መላው ሀገር ወዳድ ህዝብ እንዲመለከተውና ድርጊቱ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደሆነ እንዲያውቀው ገልጸው ለዚህ ጉዳይ የክልሉም ሆነ የፌደራል መንግስት ከተጠያቂነት እንደማይድን ተናግረዋል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply