በምስራቅ ወለጋ ያለውን ግጭት በመሸሽ ከ43 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸው ተገለጸ በምስራቅ ወለጋ አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ግጭት በመሸሽ በአጠቃላይ 43,139 ሰዎች ተፈናቅለው እንደሚገ…

https://cdn4.telesco.pe/file/p3uM5GFOACRbZOqz42a6wfuktNM0kMkwO_aCezHm2GlIbyFwOxWAOsCW9n9n7veOZJKAXerl1kXsmqctd5fB0B2XFJPmvfc6dnjVqHG65zrjTz3gmjm_yyxH1GU2uKpQ9EpOy1yyEQgZiWEYN1XXTKig5MU72UFniNKTmbU7_Dj5iOv05io9qkkdg9ePeHXalKIYc5o0pFeL2SD7Gf-WRLbEYLy1KWo77IO2VBqmFnbG2AvfjN2Yeb7roqaARpY70xCNJGSruMeQpnHbDyekVTX7HgB3h_VQdbzKRqKAp9Ag3K12PptItVNXKe3YGDlzw-n5SSF1gHuX4UsuOlrJlg.jpg

በምስራቅ ወለጋ ያለውን ግጭት በመሸሽ ከ43 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸው ተገለጸ

በምስራቅ ወለጋ አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ግጭት በመሸሽ በአጠቃላይ 43,139 ሰዎች ተፈናቅለው እንደሚገኙ የዞኑ የአስተዳደርና የፀጥታ አካላት አስታውዋል፡፡
ነዋሪዎቹ የተፈናቀሉት በምስራቅ ወለጋ በሚገኙ ,ሊሙ ፣ ጉደያ ቢላ ፣ ኪረሙ ፣ ሌቃ ዱለቻ ፣ በዲጋ ፣ እና ቸከሆሮ በሚባሉ 5 ወረዳዎች እና ጉድሩ ወለጋ ዞን ኡሙሩ ወረዳ መሆናቸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሸን (ኢሰመኮ) ከዞኑ አስተዳዳሪዎች መስማቱን ገልጿል፡፡
በተጨማሪም ወደ እነዚህ አከባቢዎች የሚያደርሱ መንገዶች አሁንም ዝግ በመሆናቸውና በአከባቢው ያለው ውጥረት አሁንም ባለመርገቡ ምክንያት ሰዎች መሰረታዊ አቅርቦቶችንና ሕክምና ለማግኘት ጭምር በከፍተኛ ችግር ላይ እንደሚገኙ ኢሰመኮ ነው የገለጸው፡፡
ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ እንዳሉት የፀጥታ አስከባሪዎች አንድን አካባቢን ለቅቀው ሲሄዱ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ዋነኛው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በቂ የፀጥታ ኃይሎች በተለይ ለግጭትና ጥቃት ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች ላይ በቋሚነት የጸጥታ ሃይሎችን መመደብ ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡
ጥቅምት 08 ቀን 2014 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ 107.8 የኢትዮጵያውያን

Source: Link to the Post

Leave a Reply