በምስራቅ ጉጂ ዞን 14 የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ ተወሰደ

በምስራቅ ጉጂ ዞን 14 የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ጉጂ ዞን ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 14 የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

እንደ ክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፃ የሽብር ቡድኑ ላይ እርምጃው የተወሰደው በዞኑ ጎሮ ዶላ ወረዳ ለጥፋት ሲንቀሳቀሱ ነው፡፡

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የሰላም ማስከበር የስራ ሂደት ኃላፊ ዋና ሳጅን ጉተማ ሳፈዮ ቡድኑ በአካባቢው እየተዘዋወረ ጉዳት እንዳያደርስ በንቃት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከጥፋት ቡድኑ አራት ክላሽ፣ አንድ ኤም-16፣ አንድ የእጅ ቦምብና አራት ትጥቅ ተይዟልም ነው ያሉት፡፡

የክልሉ ልዩ ኃይል፣ መደበኛ ፖሊስና ሚሊሻ ፀረ ሰላም ኃይሎቹን ለመደምሰስ እና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

The post በምስራቅ ጉጂ ዞን 14 የኦነግ ሸኔ አባላት ላይ እርምጃ ተወሰደ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply