በምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቡኝ ወረዳ የፖሊስ ሀይሎች በአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ የጥይት ድብደባ ማድረጋቸውን ተጎጅዎች ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 19 ቀን 2013 ዓ.ም…

በምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቡኝ ወረዳ የፖሊስ ሀይሎች በአንድ ቤተሰብ አባላት ላይ የጥይት ድብደባ ማድረጋቸውን ተጎጅዎች ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 19 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ተጎጅዎቹ ለአሻራ ሚዲያ እንደገለጹት ጷግሜ አንድ ቀን 2012 ዓ.ም ምሽት ሶስት ሰዓት ገደማ በቢቡኝ ወረዳ ፖሊሶች የሚመራ እና የአካባቢ ቡጂሌዎችን ጨምሮ ዘጠኝ የሚሆኑ የጸጥታ አካላትና ፖሊሶች በቢቡኝ ወረዳ ደብረ ዘይት በተባለ ቀበሌ ላይ ተኩስ በመክፈት በቤተሰብ አባላት ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት አድርሰውብናል ብለዋል፡፡ ጉዳዩን በቅርብ የተከታተለው ጎረቤት እንዳስረዳን የፖሊስ ሀይሎች ይህንን አሰቃቂ ድርጊት የፈጸሙት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ አላቸው በሚል የተሳሳተ መረጃ እንደሆነ ገልጸው መሳሪያው በሟች አባታቸው አቶ ደባስ ስም በህጋዊ መንገድ የተመዘገበ እና ፈቃድ ያለው ስለመሆኑ መታወቂያው ቤታቸው ድረስ አለ ሲሉ ገልጸውልናል፡፡ በጥይት ግራ እጁን ተመትቶ በአዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እጁ የተቆረጠው ደጀን ደባስ የተባለው ልጅ በሰዓቱ ቤት ውስጥ ከነበሩት የቤተሰብ አባላት በመጀመሪያ እኔን በሁለት ጥይት መቱኝ ከዚያም እናቴ በድንጋጤ እኔ ላይ ስትወድቅብኝ በአራት ጥይት የተለያዬ ቦታ ላይ መትተዋት በባህርዳር ፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ትገኛለች ሲል አስረድቶናል፡፡ አሻራ ሚዲያ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply