You are currently viewing በምስራቅ ጎጃም ዞን ባሶ ሊበን ወረዳ በስልጠና ላይ የነበሩ የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አባላት እንዲበተኑ ተደረገ፤ ድብደባ እና እስር የተፈጸመባቸው እንዳሉም ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከ…

በምስራቅ ጎጃም ዞን ባሶ ሊበን ወረዳ በስልጠና ላይ የነበሩ የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አባላት እንዲበተኑ ተደረገ፤ ድብደባ እና እስር የተፈጸመባቸው እንዳሉም ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከ…

በምስራቅ ጎጃም ዞን ባሶ ሊበን ወረዳ በስልጠና ላይ የነበሩ የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አባላት እንዲበተኑ ተደረገ፤ ድብደባ እና እስር የተፈጸመባቸው እንዳሉም ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 5 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሳቦም ትዛዙ የቴኮንዶ አሰልጣኝ ነው፤ የአማራ ህዝብ ከገጠመው ሁለንተናዊ ፈተና አኳያም አማራዊ ድርሻዬን እወጣለሁ በሚል የአማራ ህዝባዊ ኃይል የፋኖ አባላትን በተለያዩ አካባቢዎች አሰልጥኗል። ከዚህም አልፎ እነ ጀግናው አስር አለቃ ኤፍሬም አሰፋ እና ጓዶቹ 8 የሽብር ቡድን አባላትን በመጣል በተሰውበት በደቡብ ወሎ አቀስታ መርከብ ተራራ አብሮ ተሰልፎ ተዋግቷል፤ በአካባባቢውና ሸሌሎች ግንባሮች ከአንድ ወር በላይ በትግሉ ተሰልፎ ከቆዬ በኋላ ወደ ትውልድ አካባቢው ባሶ ሊበን በመመለስ ሁለተኛ ዙር የፋኖ አባላትን ስልጠና አስጀምሯል። በየጁቤ ከተማ ተገኝቶ ጥር 3 ቀን 2014 ያስጀመረው ስልጠና ግን ጥር 5 ቀን 2014 ሆንብለው አቅደው ወደ ስታዲዬም በመጡ ከ20 በላይ የጸጥታ አካላት ስልጠናው የተከለከለበት መሆኑ ይናገራል። በስፍራው በነበሩ ሰልጣኞች ላይ ድብደባ እና የአጭር ጊዜ እስር መፈጸሙን ለአሚማ ተናግሯል። የወረዳው የፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ንጉስ፣ የወረዳው አስተዳደር ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምን ይሁን እና የሚሊሻ ኃላፊው አቶ አባተ በላይነህ ከ20 በላይ የጸጥታ አካላትን ይዘው በመምጣት አባላቱን እንደበተኑ ቅሬታ ቀርቧል። መ/ር አለህኝ ንጉሴ፣ ደጉ በላይነህ እና ከባድ ልመንህ በተባሉ ሰልጣኞች ላይ ከፍ ያለ ድብደባ መፈጸሙ ተገልጧል። ላይችሉህ ገበየሁ የተባለ ወጣት ሰልጣኝም ለስልጠና ከቤቱ ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ ሲወጣ በአመራሮችና በጸጥታ አካላት ተይዞ ለ1:30 ከታሰረ በኋላ ተፈቷል። ድርጊቱ የተፈጸመው በባሶ ሊበን ወረዳ የጁቤ ከተማ ስታዲዮም አካባቢ ጥር 5 ቀን 2014 ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ መሆኑ ተገልጧል። መደበኛ የአካል ብቃት ስልጠና አታድርጉ እስከመባል መድረሱም ተሰምቷል። ፋኖ ከተደራጀ እኛም ወደ ፋኖ መግባት አለብን በሚል ማህበረሰቡ ስለሚያስቸግር ስፖርት ሜዳ ላይ እሴ መደረግ የለበትም ስለማለታቸውም ተገልጧል። ኦነግ ሸኔ በሜዘሚ፣ዘምሌ የጫራ፣ ድንጓም በኩል በ5 ቀጠና አባይ ዙሪያ ጥቃት ያደርሳል በሚል ስጋት መኖሩ ተሰምቷል። ከግንደበረት ወረዳ ፊንጭ ውሃ በሚባል ሼራ ወጥረው ከፍተኛ ዝግጅት እያደረጉ ነው፣ የቡድን መሳሪያም ይተኩሳሉ ኦነጎች፣በግልጽ ሼራ ወጥረው ስልጠና የጀመሩት መስከረም ላይ ነው። ፊንጭ ውሃ ስኳር ፋብሪካ አካባቢ በርካታ የአማራ ወጣቶች በኦነጎች እንደሚገደሉ ይታወቃል። ወረዳው በ5 አቅጣጫዎች ከፍተኛ የኦነግ ሸኔ የወረራ ስጋት ያለበት መሆኑን የገለጹት የሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ አባተ በላይነህ ድብደባ አልፈጸምንም ሲሉ አስተባብለዋል። የባሶ ሊበን ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊው ምላሽ ለመስጠት አልፈቀዱም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply