You are currently viewing በምስራቅ ጎጃም ዞን የማቻክል እና የአማኑኤል ከተማ የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አስተባባሪ የነበረውና በህልውና ዘመቻው ታሪካዊ ኃላፊነቱን የተወጣው ወጣት ታስሯል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

በምስራቅ ጎጃም ዞን የማቻክል እና የአማኑኤል ከተማ የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አስተባባሪ የነበረውና በህልውና ዘመቻው ታሪካዊ ኃላፊነቱን የተወጣው ወጣት ታስሯል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚ…

በምስራቅ ጎጃም ዞን የማቻክል እና የአማኑኤል ከተማ የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አስተባባሪ የነበረውና በህልውና ዘመቻው ታሪካዊ ኃላፊነቱን የተወጣው ወጣት ታስሯል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 11 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ጎጃም ዞን ለአሚማ የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው የማቻክል እና የአማኑኤል ከተማ የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አስተባባሪ የነበረው ፋኖ አስማማው ሞላ ታስሯል። ፋኖ አስማማው በጦርነቱ ወቅት በመዝመት ታሪካዊ ግዴታውን የተወጣው ወጣት መሆኑ ተገልጧል። ግንቦት 9/2014 ዓ/ም ከምሽቱ 12:00 ገዳማ በአማኑኤል ከተማ መታሰሩን ፋኖ አስማማው አስታውቋል ተብሏል። እስሩ የተፈጸመውም በአማኑኤል ከተማ የብልፅግና ኃላፊ በሆነው በአቶ አማረ ሰውነት የሚሉት ምንጮች አሁን ላይ ፋኖ አስማማው በማቻክል ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ታስሮ ይገኛል ሲሉ አክለዋል፡፡ በተመሳሳይ ዘላለም ጫኔ የተባለ የወሎ ዩኒቨርሲቲ መምህር ቤተሠብ ለመጠየቅ ቤተሠቦቹ ወዳሉበት ምሥራቅ ጎጃም ዞን ባሶሊበን ወረዳ በመጣበት ወቅት ፋኖን ትደግፋለህ ተብሎ በተመሳሳይ ቀን ታስሮ ወደ ደብረ ማርቆስ መወሰዱ ታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply