You are currently viewing በምስራቅ ጎጃም ዞን የአማራ ህዝባዊ ኃይል ፋኖ አመራር እና አባላትን ማሳደዱ እንደቀጠለ ነው፤ በአዋበል ወረዳ የፋኖ አባል መሆኑን የገለጸው ሸጋው ይግዛው በሌሊት የግድያ ሙከራ እንደተደረገበ…

በምስራቅ ጎጃም ዞን የአማራ ህዝባዊ ኃይል ፋኖ አመራር እና አባላትን ማሳደዱ እንደቀጠለ ነው፤ በአዋበል ወረዳ የፋኖ አባል መሆኑን የገለጸው ሸጋው ይግዛው በሌሊት የግድያ ሙከራ እንደተደረገበ…

በምስራቅ ጎጃም ዞን የአማራ ህዝባዊ ኃይል ፋኖ አመራር እና አባላትን ማሳደዱ እንደቀጠለ ነው፤ በአዋበል ወረዳ የፋኖ አባል መሆኑን የገለጸው ሸጋው ይግዛው በሌሊት የግድያ ሙከራ እንደተደረገበት አስታውቋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 21 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ጎጃም ዞን የአማራ ህዝባዊ ኃይል ፋኖ አመራር እና አባላትን ማሳደዱ እንደቀጠለ መሆኑ ተገልጧል። ይህንን የማሰር እና የማሳደድ ወንጀል እየፈጸመ ያለውም በአማራ ክልል መንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ ከሆድ እና ከወንበር ውጭ ለማየት ያልፈቀዱና የማይችሉ አይለወጤ ካድሪዎች እንደሆነም ለአሚማ የደረሱ ቅሬታዎች አመልክተዋል። በአዋበል ወረዳ የፋኖ አባል መሆኑን የገለጸው ሸጋው ይግዛው ደግሞ ሀገር ሰላም ብሎ እንደለመደው በሌሊት ወጥቶ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ በሩን ከፍቶ ሲወጣ ከመቅጽበት በአንድ ጥይት የግድያ ሙከራ እንደተደረገበት ገልጧል። በወቅቱም ፋኖ ሸጋው መሬት ላይ መውደቁንና እንደፈጣሪ ፍቃድ መትረፉን አውስቷል። በጥይት የተመታውን የቤቱን ግድግዳም ለአሚማ ከተላከው ፎቶ ለማየት ተችሏል። በወቅቱም ከግቢው ውጭ “ተበላህ” የሚል ድምጽ መስማቱን ፋኖ ሸጋው ተናግሯል። ይህን የግድያ ሙከራ ከማድረጋቸው በፊት የብልጽና ካድሪዎች በተለያዩ ጊዜያት ለማስፈራራት ይሞክሩ እንደነበር አውስቶ ይህ ሁሉ አካሄድ የያዝኩት አቋም ትክክል መሆኑን ስለሚያሳየኝ አጠናክሬ እቀጥልበታለሁ ብሏል። በማስፈራራትና ጨለማን ተገን በማድረግ በድብብቆሽ የከሰርቶ መንገድ በሚፈጸም ግድያ የሚቆም አንዳች ህዝባዊ ትግል አለመኖሩንም መታወቅ አለበት ተብሏል። ይህ የግድያ ሙከራ የተደረገው ያሳለፍነው አርብ የካቲት 18 ቀን 2014 ከሌሊቱ አስር ሰዓት ተኩል ሲሆን ፋኖ ሸጋው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለመስራት ከቤቱ በሚወጣበት ወቅት መሆኑ ታውቋል። ፋኖ ሸጋው ይግዛው በእለቱም ለአዋበል ወረዳ ለ01 ቀበሌ ጽ/ቤት የተፈጸመውን የግድያ ሙከራ በተመለከተ ሪፖርት ማድረጉን ጠቁሟል። የአማራ ህዝብ እና የለውጥ ትግሉ ያገባናል የሚሉ ወገኖች በሙሉ በአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አባላት ላይ በብልጽግና ካድሪዎች ትዕዛዝ ሰጭነት እየተደረገ ያለውን ወከባ፣ እስር፣ማሳደድና የግድያ ሙከራን በማውገዝ በተሳሳተው እና ጸረ የአማራ አደረጃጀት በሆነው የአይለወጤዎች አካሄድ ላይ በአስቸኳይ የእርምት እርምጃ ይወሰድ ዘንድ እንዲሰሩ ተጠይቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply