You are currently viewing በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤሊያስ ወረዳ በገዳም ውስጥ እያሉ ጥቃት የተፈጸመባቸው ነዋሪዎች ህክምና እያገኙ ባለመሆኑ ለከፍተኛ ስቃይ መዳረጋቸው ተገለጸ፤ የግፍ እስረኞች ቁጥርም ከእለት እለት…

በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤሊያስ ወረዳ በገዳም ውስጥ እያሉ ጥቃት የተፈጸመባቸው ነዋሪዎች ህክምና እያገኙ ባለመሆኑ ለከፍተኛ ስቃይ መዳረጋቸው ተገለጸ፤ የግፍ እስረኞች ቁጥርም ከእለት እለት…

በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤሊያስ ወረዳ በገዳም ውስጥ እያሉ ጥቃት የተፈጸመባቸው ነዋሪዎች ህክምና እያገኙ ባለመሆኑ ለከፍተኛ ስቃይ መዳረጋቸው ተገለጸ፤ የግፍ እስረኞች ቁጥርም ከእለት እለት እየጨመረ መሆኑ ተመላክቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 30 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ጎጃም ዞን የሚገኘው የደብረ ኤሊያስ ወረዳ የሊቃውንት መፍለቂያ አካባቢ ስለመሆኑ ይታወቃል። እንደአብነትም:_ 1) የጻዲቁ ተክለ አልፋ የትውልድ አካባቢ፣ 2) የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ የሆነበሩት የአቡነ ቴዎፍሎስ የትውልድ አካባቢ፣ 3) የፍቅር እስከ መቃብር ደራሲ የሀዲስ አለማየሁ ቀዬ፣ 4) የእነ ዮፍታሄ ንጉሴ ሀገር እንዲሁም የእነዚህ እና የሌሎች በርካታ ሊቃውንት ሀገር መሆኑ ይታወቃል። ዳሩ ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ታሪክ ጠል እና አጥፊ በሆኑ የዘመኑ ጉዶች/ካድሪዎች ሀገራችን በከፍተኛ ችግር ላይ በወደቀችበት በአሁኑ ሰዓት እንኳ ገዳምን እና ገዳማውያንን ለማጥፋት አቅደው እየሰሩ መሆናቸው ሲታይ በእጅጉ አሳዛኝ ጊዜ ላይ ስለመድረሳችን በነዋሪዎች ዘንድ እንደ ግልጽ ማሳያ ተደርጎ ተገልጧል። በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤሊያስ ወረዳ ብሄረ ብጹአን አጼ መልክአ ስላሴ አንድነት ገዳም በግፍ የተገደሉ ሰዎች ቁጥርን በተመለከተ እስካሁን ባለን መረጃ 7 ጸበልተኛ እና 11 አርዲት እናቶች በድምሩ ከ18 በላይ ሰዎች በጥይት ሲገደሉ፣ የቆሰሉት ደግሞ ከ30 በላይ መድረሳቸው ተነግሯል። ነገሩ ከቀን ወደ ቀን አሳሳቢ ሆኗል የሚሉት ምንጮች በርካቶች ያለፍትህ ከመታሰራቸው ባሻገር ሙሉ ጸበልተኛው ከገዳሙ በኃይል እንዲወጣ መደረጉ ስርዓቱ ገዳሙን ለማፍረስ አቅዶ እየሰራ ስለመሆኑ አመላካች ነው ሲሉ ተናግረዋል። በግፍ የታፈኑ አገልጋዮች እና አባቶች እስካሁን ያሉበት ካለመታወቁም በላይ የቆሰሉት ሰዎች ህክምናም አላገኙም፤ ጥይቱ ከጭንቅላታቸውና ከሰውነታቸው አልወጣም፤ ማንም ሠው ቀርቦ ይህን ጉዳይ እንዳያይ እና እርዳታ እንዳያደርግ የፀጥታ ሃይሉ ገዳሙ ላይ ከበባ በማድረግ እና እርዳታ እንዳያገኙ በማድረግ አፍነዉ ይዘውት እንደሚገኙ ይታወቅልን ሲሉ ነዋሪዎች ጥሪ አድርገዋል። ቁስለኞችና የተጎዱት ወገኖች ምንም እንኳ ከቆሰሉ አራት ቀናት ቢሆናቸውም በአስቸኳይ ህክምና እንዲያገኙ አምቡላንስ የሚልክ መንግስታዊ አካል አልተገኘም ሲሉ በእጅጉ ማዘናቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል፤ አሁንም የድረሱልን ጥሪ እያቀረቡ ነው። ተጨማሪ ኃይል እንዲገባ ከተደረገ በኋላ በገዳሙ ይኖሩ ከነበሩ ጸበልተኞች መካከል በግምት ከ1,000 በላይ የሚሆኑት ናቸው በኃይል ከገዳሙ እንዲወጡ የተደረጉት ተብሏል። ከጥር 24/2015 ምሽት ጀምሮ በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤሊያስ ወረዳ ብሄረ ብጹአን አጼ መልክአ ስላሴ አንድነት ገዳም በግፍ በመታሰር ላይ የሚገኙት:_ 1) የገዳሙ አባቶች እና ምዕመናን፣ 2) ለጸበል እና ለስራ የሚሄዱ ምዕመናን እንዲሁም 2) የገዳሙ አማኞች እና ቤተሰቦቻቸው ናቸው። እስሩ፣ አፈናው እና ግድያም ጭምር እየተፈጸመ ያለው በዋናነት በምስራቅ ጎጃም ዞን እና በደብረ ኤሊያስ ወረዳ መስተዳድር ስምሪት በተሰጣቸው የሚሊሻ እና የፖሊስ አባላት ይሁን እንጅ ከክልል በተላኩ በልዩ ኃይል አባላት አማካኝነትም ተፈጽሟል። እየታሰሩ የሚገኙትም በደብረ ኤሊያስ ከተማ እና ጓይ ቀበሌ ሲሆን ጥር 24/2015 ማታ ላይ የታፈኑት 3 አባቶች አድራሻ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ አልታወቀም። 17 ዓመት ከገዳም ወጥተው የማያውቁት እና አፈና ከተፈጸመባቸው በኋላ አድራሻቸው በትክክል ያልታወቁ 3 የገዳም አባቶችም:_ 1) የገዳሙ ዋና አስተዳዳሪ/አበምኔት ቆሞስ አባ ኤልሳ ደመቀ፣ 2) አባ ክንፈ ሚካኤል እና 3) አባ ገ/መድህን ናቸው። የእነዚህ አባቶች አድራሻ በትክክል እንዲታወቅ፣ ተገድለውም ከሆነ በትክክል ለህዝብ መርዶ እንዲነገረው ተጠይቋል። የወረዳ ካድሪዎችም በተጨፈጨፉት ገዳማውያን ነፍስ እንጠየቃለን የሚል ስጋት ስላደረባቸው አስቀድመው ከተጠያቂነትን ለማምለጥ እየሞከሩ ነው። ይኸውም ጥር 28/2015 በተደረገው በእየእድሩ በተጠራው ስብሰባ ያልተገኘ አንድ ሺህ ብር ይቀጣል በማለት የደብረ ኤሊያስ ነዋሪዎችን አስገድደው ሰብስበው ነበር። የስብሰባቸው ዋነኛ አላማም:_ 1) ጥቃት የደረሰበትን ገዳም እና አባቶችን እንደ ወንጀለኛ ማሳዬት ነው፤ 2) በውሸት ማህበረሰቡ በገዳሙ እንደተጎዳ አድርጎ በማሳዬትና ጫና በመፍጠር ተቃውሞ እንዲወጣ እና ለበላይ አካል ድምጽ እንዲያሰማ ብሎም ይፍረስ በሚል እንዲወሰን ጫና ማድረግ ነው። 3) ገዳሙ ከፈረሰ አርሶ አደሩን የመሬት ተጠቃሚ ሊያደርጉት እንደሚችሉ በመግለጽ ደጋፊ ለማድረግ መሞከር ነው፤ እንዲሁም 4) በተፈጸመው ጭፍጨፋ ተጠያቂ ላለመሆን የማምለጫ መንገድን ለማመቻቸት የተዘየደ ሴራ ነው ብለውታል_ነዋሪዎቹ። ይህ እየሆነ ያለው ከገዳማትም ይሁን ከሌሎች የእምነት ተቋማት በተለዬ መልኩ በግሉ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ያለው እና በእያመቱ በመስኖ አራት ጊዜ ለማምረት የሚችል አቅም እንዳለው በስፋት የተዘገበለት ገዳም መሆኑ ይታወቃል። ይህ ገዳም እና ገዳማውያውን ማህበረሰቡን አልጠቀሙ ሆኖ ሳይሆን አንዳንድ የደብረ ኤሊያስ ወረዳ እና የምስራቅ ጎጃም ዞን አመራሮች በጥቅም የተሳሰሩ በመሆናቸው ነው ተብሏል። ለዚህም ነዋሪዎች እንደማሳያ የጠቀሱት:_ 1) የገዳም አባቶችን ከአሰራሩ ውጭ ገንዘብ እንዲሰጧቸው ያደረጉት ጥረት ባለመሳካቱ ቅሬታ ስላደረባቸው፣ 2) ሃምሌ 6/2014 ወደ ገዳሙ ለክብረ በዓል ከሄዱ ምዕመናን መካከል ከ30 መኪና በላይ ተጓዥ እንዲዘረፍ አስደርገው፣ መረጃው በዞን አጣሪ ቡድን ከተጣራ እና ከተመሰከረባቸው በኋላ በአንዳንድ የጥቅሙ ተጋሪ በሆኑ የዞን አመራሮች ጫና ክሱ የተቋረጠ/የተተወ መሆኑና 3) በጥቅምት 2015 በደብረ ኤሊያስ ከተማ የሜዚን አካባቢ ሙስሊሞች በሚያከብሩት የአባ ፋቄ ክብረ በዓል ለመገኘት የመጡ አማኞችን በቀን እንዲዘረፉ ማድረጋቸውና ተጠያቂነትም አለማስፈናቸው፤ ስርዓት አልበኝነትና በጥቅም መተሳሰረር እንዳለ ሌላኛው ማሳያ አድርገው ወስደዋል። የወረዳው አመራሮች ባደረጉት ጫና ህዝቡ ጥር 25/2015 ሰላማዊ ሰልፍም እንዲወጣ ተደርጓል። በደብረ ኤሊያስ ከተማ፣ በጓይ ታዳጊ ከተማ እና በደብረ ማርቆስ ማ/ቤት በግፍ ከታሰሩት በትንሹ ከ70 በላይ ገዳማውያን ፣በተሰቦች እና ጸበልተኞች መካከል:_ 1) በዛብህ ወርቁ፣ 2) ሞላ ደምስ፣ 3) ሞላ አንለይ፣ 4) ጸጋዬ ፈረደ፣ 5) ግዛቸው መሰሉ፣ 6) ጥላሁን ተስፌ፣ 7) ወ/ሮ አዳም (ሴት)፣ 8 ወ/ሮ ጥሩዬ ዳኛቸው፣ 9) ወ/ሮ እርስቴ፣ 10) የአቶ ደባስ አበበ ባለቤት፣ 11) የአቶ ይሁን ባለቤት፣ 12) የአቶ ድረስ አለማየሁ ባለቤት፣ 13) የአቶ አወቀ ባለቤት፣ 14) የአቶ ንጉሴ ባለቤት፣ 15) የአቶ ነጋ መኮንን ባለቤት ወ/ሮ የአልጋ ቢተው የ2 ዓመት ህጻን የያዘች እናት እና ሌሎችም ይገኙበታል። ወደ ባ/ዳር ሄደው አቤቱታ በማቅረባቸው ብቻ እንደ ወንጀለኛ ተቆጥረው ካለምንም ህጋዊ የመበርበሪያ ሰነድ/ የፍርድ ቤት ደብዳቤ በኃይል ቤታቸው ከተፈተሸባቸው እና ቤተሰባቸውን በትነው በየጫካው እየተሳደዱ ከሚገኙት የደብረ ኤሊያስ የ01 ቀበሌ ነዋሪዎች መካከል:_ 1) አቶ ጌታነህ በላይ፣ 2) አቶ አወቀ ውብሸት፣ 3) አቶ አማን አይናለም፣ 4) አቶ ስንታየሁ ቁሜ፣ 5) አቶ ሞላ ስመኝ፣ 6) አቶ ነብይ እና ሌሎችም ይገኙበታል። የተፈለጉት ሰዎች ባለመገኘታቸው ከጥር 24/2015 ጀምሮ ቤታቸው በአገዛዙ የአፈና አስፈጻሚዎች በከበባ ላይ የሚገኙ እንዳሉ ተሰምቷል። አጣሪ ቡድን ከባህር ዳር ይመጣል መባሉን ተከትሎ ከደብረ ኤሊያስ እስር ቤት ብዙዎችን አስወጥተው ወደ ጓይ ታዳጊ ከተማ እንደወሰዷቸው ተመላክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply