You are currently viewing በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አሞራ ቤት ቀበሌ በተፈጸመው ጥቃትና ራስን ለመከላከል በተሰጠው የአጸፋ ምላሽ ላይ አልሞት ባይ ተጋዳዩን ገልብጦ እንደ ወንጀለኛ እና ከፋፋይ ለማሳየት እየተሞከረ ነው…

በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አሞራ ቤት ቀበሌ በተፈጸመው ጥቃትና ራስን ለመከላከል በተሰጠው የአጸፋ ምላሽ ላይ አልሞት ባይ ተጋዳዩን ገልብጦ እንደ ወንጀለኛ እና ከፋፋይ ለማሳየት እየተሞከረ ነው…

በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አሞራ ቤት ቀበሌ በተፈጸመው ጥቃትና ራስን ለመከላከል በተሰጠው የአጸፋ ምላሽ ላይ አልሞት ባይ ተጋዳዩን ገልብጦ እንደ ወንጀለኛ እና ከፋፋይ ለማሳየት እየተሞከረ ነው በሚል ብዙዎች ተቃውሞ እያቀረቡ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አሞራ ቤት ቀበሌ አውራ ጎዳና አካባቢ በተፈጸመው ጥቃትና ራስን ለመከላከል በተሰጠው የአጸፋ ምላሽ ላይ አልሞት ባይ ተጋዳዩን ገልብጦ እንደ ወንጀለኛ እና ብሄር ከብሄር ለማጋጨትና ለመከፋፈል እንደሰሩ ለማሳየት እየተሞከረ ነው በሚል ለቀረበው አገላለጽ ተቃውሞ እየቀረበበት ነው። ብዙዎች የአባዬን እከክ ወደ እምዬ ለከክ፣ ፍዬል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ፣ አህያውን ትቶ ዳውላውን አይነት አካሄድ በዘላቂነት ለምንም ለማንም እንደማይጠቅም በተለያየ መንገድ ለአሚማ እየገለጹ ነው። በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አሞራ ቤት ቀበሌ አውራ ጎዳና እየተባለ በሚጠራው አከባቢ ትላንት ከቀኑ ሰባት ሰዓት ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች በከፈቱት ተኩስ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል ሲል ፋና ዘግቧል፡፡ አስተዳዳሪው አቶ ታደሰ ቦሰት አስቀድሞ ለአሚማ እንደገለጹት ከኦሮሚያ በናዝሬት በኩል አድርገው ወደ ምንጃር ሸንኮራ በ3 ተሽከርካሪ የመጡ የቡድን መሳሪያ የያዙ ታጣቂዎች አሞራ ቤት ቀበሌ አውራ ጎዳና አካባቢን ሁለት ሶስት ጊዜ ተዘዋውረው ቅኝት ካደረጉ በኋላ በቅድሚያ ቡና ሲጠጡ በነበሩ በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ቀጥታ ተኩስ በመክፈት አንድ በመግደል፤ ሁለተኛውን በከባድ አቁስለዋል። በመቀጠልም መሀል አስፓልት ላይ በመሆን ወደ ግራ እና ወደ ቀኝ የጅምላ ተኩስ በመክፈት በህጻናትና በሴቶች ላይ ጉዳት አድርሰዋል ብለዋል። በዚህም አንድ ሚሊሻ እና አንድ የፌደራል ፖሊስ ህይወታቸው ስለማለፉ 4 ህጻናትና ሴቶችም በጥቃቱ ስለመቁሰላቸው ነግረውናል። በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አሞራ ቤት ቀበሌ አውራ ጎዳና ላይ ያልታወቁ ሰዎች ጥቃት ፈጸሙ ብሎ የዘገበው ፋና ተመልሶ በምስራቅ ሸዋ ዞን ቆርኬ/አውራ ጎዳና ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ ለኦፕሬሽን ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የክልሉ ሚሊሻ አባላት ላይ በምንጃር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ኃይሎች ባደረሱት ጥቃት በርካታ የፀጥታ አባላት መሞታቸውን የዞኑ አስተዳደር ገልጧል ሲል ዘግቧል። ፋና እንደገናም በምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ጥቃት በደረሰበት ቦታ ላይ ክትትል በማድረግ ወንጀለኞችን ለሕግ ለማቅረብ እየተሠራ ነው ሲልም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትን በመጥቀስ ዜና ሰርቷል። ለኦፕሬሽን ስራ ሲጓዙ ነበር ያላቸውን አካላት በእነዚህ ጽንፈኛ ኃይሎች እኩይ ተግባርና ሴራ የአማራና የኦሮሞ ህዝቦች ዘላቂ አብሮነትና ሁለንተናዊ ብልጽግና ጉዞን ለማደናቀፍ የተወጠነ የጥፋት ዕቅድ አካል መሆኑን እንገነዘባለን እንዲሁም በድርጊቱ ተሳትፈዋል ያላቸውን የምንጃር ጽንፈኛ ሲል የጠራቸውን አካላት በቁጥጥር ስር ለማዋል ከአማራ ክልል መንግስት ጋር አብሮ እየሰራ ስለመሆኑም ዘግቧል። የአማራ ክልል መንግስት ባወጣው መግለጫም “ምንም እንኳን ከወራሪው ኃይል ጋር በከፊል ጦርነት ውስጥ መሆናችን የሚዘነጋ ባይሆንም ጎን ለጎን በሕዝቦች መካከል በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጽናት የሚያስችሉ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትና አያሌ የምክክር መድረኮችን እያከናወነ መሆኑም ይታወቃል።” ይላል። ይሁን እንጂ አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን ውላጅ የሆኑ ተስፈኛ ጽንፈኞችና አሸባሪዎች (የባለቤቱን ስም ለመግለጽ ያልደፈረ ነው) በአማራ ክልል ሕዝብ እና በአጎራባች ክልል ሕዝብ መካከል ግጭት ለመፍጠርና የክልሉን ሕዝብ ማኅበራዊ እረፍት ለመንሳት በክልላችን አንዳንድ አካባቢዎች ግጭት ለማጫር ተንቀሳቅሰዋል፤ እየተንቀሳቀሱም ይገኛሉ ብሏል። ጽንፈኛና ፀረ ሰላም ቡድኖችን (እነማን እንደሆኑ አልገለጸም) አደብ ለማስገዛት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎችና የህግ የበላይነትን የማስከበር መንግሥታዊ ስምሪት ሆን ተብሎ በሚለቀቅ የተሳሳቱ መረጃዎች (በማን በኩል እንደተለቀቁ በይፋ አልገለጸም) ሕዝቡ ሳይወዛገብ በሰብአዊነት ላይ የሚፈፀም ወንጀልን ለመከላከል የዜግነት ድርሻችሁን እንድትወጡ የክልሉ መንግሥት በአክብሮት ይጠይቃል ነው ያለው። በሌላ በኩልም በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ከጽንፈኛና ፀረ ሰላም ኃይሎች ጋር ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ የጥፋት ትስስር በመፍጠር የአማራ ክልልን የቀውስ ሜዳ ለማድረግ፤ የክልሉን ሕዝብ ማኅበራዊ እረፍት ለመንሳት እንዳሁም የህዝባችንን ሰላምና የመልማት እድል በመንፈግ ከድህነት እንዳይወጣ ለማድረግ ታልሞ የተዘጋጀን የጠላት እቅድ በመፈጸምም ሆነ በማስፈጸም እኩይ ተግባር ውስጥ የተዘፈቃችሁ አካላት ከድርጊታችሁ እንድትታቀቡ የአማራ ክልል መንግሥት በጥብቅ ያሳስባል ብሏል። ያም ሆነ ይህ በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አሞራ ቤት ቀበሌ አውራ ጎዳና አካባቢ የተፈጸመውን ጥቃት በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ እንደተፈጸመ አድርጎ የማቅረብ እና በመግለጫ ወደ ራስ የመጠቅለል ሁኔታ ተስተውሏል። ከእያቅጣጫው የተሰጡ መግለጫዎች ግልጽ ጥቃት የተፈጸመባቸውን እና ራሳቸውን ለመከላከል በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ታግለው የህጻናትንና የሴቶችን እልቂት በቀነሱት ምንጃሮች ላይም ሆነ በአንድም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ደግፋችኋል ባሏቸው በሌሎች የውስጥና የውጭ ብለው በፈረጇቸው አካላት ላይ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆናቸውን ያመለክታል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply