You are currently viewing በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ተጠልለው የሚገኙ ወገኖች ከዞን እስከ ክልል እና ፌደራል ያሉ አካላት ድጋፍ እያደረሱን አይደለም ሲሉ አማረሩ። አማራ ሚዲያ ማ…

በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ተጠልለው የሚገኙ ወገኖች ከዞን እስከ ክልል እና ፌደራል ያሉ አካላት ድጋፍ እያደረሱን አይደለም ሲሉ አማረሩ። አማራ ሚዲያ ማ…

በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ተጠልለው የሚገኙ ወገኖች ከዞን እስከ ክልል እና ፌደራል ያሉ አካላት ድጋፍ እያደረሱን አይደለም ሲሉ አማረሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ አልጌ ከተባለ ቀበሌ በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ ተፈናቅለው በምንጃር ሸንኮራ አረርቲ ቴክኒክ እና ሙያ ት/ቤት የሚገኙ ወገኖች ለከፋ ሁለንተናዊ ችግር ከተጋለጡ አራት ዓመታትን አስቆጥረዋል። ታዲያ በቆይታቸው ከዞን እስከ ክልል እና ፌደራል ያሉ አካላት ድጋፍ እያደረሱን አይደለም ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል። አቤቱታችን በተደጋጋሚ እያቀረብን ቢሆንም ተገቢ ምላሽ እያገኘን አይደለም ብለዋል። ለጋሽ ድርጅቶችም ወደ ምንጃር አረርቲ እየመጡ ባለመሆኑ ተረስተናል የሚሉት አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ያነጋገራቸው ተጎጅዎች በወረዳው ከ2,600 በላይ የተፈናቀሉ ወገኖች እንዳሉ ጠቁመዋል። በአንጻሩ በሰሜን ሸዋ ዞን የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ እና የአረርቲ ከተማ አስተዳደር ለዘመናት ከሚኖሩበት ቀያቸው ከዘር ጭፍጨፋ ተርፈው ለመጡ ወገኖች ከጎናቸው በመሆን አቅማቸው በፈቀደ መጠን ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ በመጥቀስ ምስጋና ቀርቦላቸዋል። በተጨማሪም የአረርቲ ቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅም እየተቸገረም ቢሆን ግቢውን በመፍቀድ ከጎናቸው ባለመለዬቱ ተመስግኗል። አሁን ላይ በአረርቲ ቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ግቢ ብቻ :_ ወንድ 88፣ ሴት 89፣ በድምሩ 177 የሚሆኑ ከጥቃት የተረፉ አማራዎች በችግር ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል። ከመካከላቸውም:_ 31 የወገንን ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎች ሲሆኑ፣ 2 የሚያጠቡ እናቶች፣ 5 ደግሞ በህክምና ክትትል ላይ ያሉ ተፈናቃዮች ስለመኖራቸው ተገልጧል። ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን በተለይም ከቦሰት፣ከመተሃራ ፈንታሌ፣ አልጌ እና አካቢው በተለያዩ ጊዜያት አማራ ተኮር ጭፍጨፋ እና መፈናቀል እየተፈጸመ መሆኑን የሚገልጹ ነዋሪዎች አሳሳቢ ለሆነው ችግር አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጠው በተደጋጋሚ እየጠየቁ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply