በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ እና አረርቲ ከተማ አስተዳደር የፋኖ አደረጃጀት ሰልጣኞች ሲከታተሉት የቆዩትን ወታደራዊ ስልጠና አጠናቀዉ ተመረቁ፡፡ ታህሳስ 04/2014/አሻራ ሚዲያ / በወረዳዉና በከ…

በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ እና አረርቲ ከተማ አስተዳደር የፋኖ አደረጃጀት ሰልጣኞች ሲከታተሉት የቆዩትን ወታደራዊ ስልጠና አጠናቀዉ ተመረቁ፡፡ ታህሳስ 04/2014/አሻራ ሚዲያ / በወረዳዉና በከተማ አስተዳደሩ ፋኖ አደረጃጀት ስር ታቅፈዉ ወታደራዊ ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ 403 ሰልጣኞች በትናንትናዉ ዕለት የምረቃ ሥነ-ስርዓታቸዉ ተካሂዷል፡፡ በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይም የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ እና የአረርቲ ከተማ አስተዳደር ማህበረሰቦች፣ የአመራር አካላት እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች እና የፋኖ አደረጃጀት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ ሰልጣኝ ፋኖ ወጣት ማህሌት ሻምበል ፋኖ ማለት ለህዝብ የሚሞት፣ የሚቆም፣ ከህዝብ በፊት በመቅደም በህዝብ ላይ የሚደርስ መከራ፣ ሀዘንና ሰቆቃን ለማስቀረት የሚታገል ነዉ ብላለች፡፡ ፋኖን በመቀላቀል ለህዝብ ለመታገል ዓላማ ስለነበ…ረኝ ስልጠናዉ አልከበደኝም የምትለዉ ወጣት ማህሌት እንደጁንታዉ ያለ ደካማ ሀገር አፍራሽ ቀርቶ የጠነከረ አፍራሽ ሀይል ቢኖር አንበገርም በምንከፍለዉ ዋጋም ደስተኛ ነን ብላለች፡፡ የወረዳዉ ፋኖ አሰልጣኝ የሆኑት ሃምሳ አለቃ ይርጋ በበኩላቸዉ የወረዳዉና የከተማ አስተዳደሩ ወጣቶች በራሳቸዉ ተነሳሽነት የአቅም ግንባታ ስፖርቶችንና የወታደራዊ ስልቶችን ስልጠና በመዉሰድ በማጠናቀቅ 403 የሚሆኑ ወጣቶች መመረቅ ችለዋል ብለዋል፡፡ በስልጠናዉ የቡድን መሳሪያ ትዉዉቅ፣ የመሳሪያ ተኩስና ሌሎችም የዉጊያ መሳሪያዎች አጠቃቀም ወጣቶቹ ማግኘታቸዉን ጠቁመዋል፡፡ ወጣቶች በራሳቸዉ ተነሳሽነት ወደ ፋኖ በመቀላቀል ስልጠና መዉሰዳቸዉ የአማራ መሳደድ፣ ሞት ይብቃ በሚል ነዉ ያሉት ሃምሳ አለቃ ይርጋ ይህ ስልጠና በስኬት እንዲጠናቀቅ ድጋፍና ትብብር ላደረጉ የወረዳዉና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች እና የማህበረሰብ አካላት ከፍተኛ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል የሰሜን ሸዋ ፋኖ አደረጃጀት ኦዲተርና የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ፋኖ አደረጃጀት ሰብበሳቢ ታደሰ ፍቅረ እንደገለፁት ፋኖ ማለት ከአማራ አብራክ የወጣ የጀግና ስብስብ ነዉ ብለዋል፡፡ ፋኖ ምንም ዓይነት ደመወዝ ሳይከፈለዉ ለኢትዮጵያ ህዝብ የቆመ የጀግና ስብስብ መሆኑን አቶ ታደሰ ተቁመዉ በአሁኑ ሰዓት ለሀገር አንድነት ከመንግስት ጎን ሆኖ እየታገለ ያለና በቀጣይም የሚታገል መሆኑን አንስተዋል፡፡ ፋኖ ሀገር አፍራሾችን ፣ ህፃናትንና ሽማግሌዎችን በግፍ የሚገደልን ይጠላል ያሉት ሰብሳቢዉ ምንግዜም ግንባር ቀደም ለሀገራችን አንድነት ከተለያዩ የጸጥታ አካላት ጋር ሆኖ ይታገላል ብለዋል፡፡ አያይዘዉም ስልጠናዉ በስኬት ለመጠናቀቅ እንዲችል ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋናቸዉን አቅርበዋል፡፡ የምርቃቱ የክብር እንግዳ የሆኑት ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ በበኩላቸዉ ፋኖ ከሺህ ዓመታት በፊት ዘመናዊ ጦር በሌለበት ሰዓት በአርበኝነት ሀገሩን ያስከበረ ነዉ ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የተለያዩ የመንግስት የፀጥታ ሀይሎች በአሉበት ሰዓትም ቢሆን ጠላቶቻችን የበዙ በመሆናቸዉ ፋኖ የሚከፍለዉ ዋጋ ለሀገር አንድነት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ፋኖ ማለት ደመወዝ ቁረጡልኝ፣ ጡረታ ያዙልኝ ሳይል በራሱ ትጥቅ ለሀገር አንድነት የሚዋደቅ ህዝባዊ ሀይል ነዉ ያሉት ዶ/ሩ፡፡ ፋኖ ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተሳስሮ የተቋቋመና በሕግና በስርዓት የሚመራ ነዉ ያሉት የክብር እንግዳዉ ሕዝቡም ከጎኑ በመሆን ስንቅ በማቀበልና በሌሎችም ድጋፎች ሊያጠናክረዉ ይገባል ብለዋልሲል ዘገበው የምንጃር ኮምንኬሽ ነዉ ፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply