በምክር ቤቱ ህንጻ የአመጽ ጥቃት ላይ የተሳተፈው ሰው ተፈረደበት

በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ህንጻ ላይ እኤአ ጥር 6/2020 በደረሰ የአመጽ ጥቃት ተሳታፊ በመሆን አንድ የፖሊስ ባልደረባ ላይ ጥቃት የፈጸመ አንድ ሰው፣ ወደ አራት ዓመት የተቃረበ፣ የ3 ዓመት ከ10 ወራት እስር የተፈረደበት መሆኑ ተገለጸ፡፡

ውሳኔው የተላለፈበት ዴቪድ ቶምሰን የተባለው የ28 ዓመት ወጣት በጻፈው ደብዳቤ፣ መጸጸቱን አስታውቋል፡፡ 

በወቅቱ ከሌሎች ባልደረቦቹ ጋር ሆኖ የምክር ቤቱን ህንጻ ሰብረው የገቡ ሰዎችን ለ2 ሰዓታት ያህል ይታገሉ በነበሩ ፖሊሶች ላይ ባደረሰው ጥቃት ይቅርታ መጠየቁ ተመልክቷል፡፡

ዴቪድ እስራት ለፈረዱበት ዳኛም፣ በፈጸመው ድርጊት መጸጸቱን የሚገልጽ ደብዳቤ ማስገባቱም ተገልጿል፡፡ 

ውሳኔውን የሰጡት የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሮይስ ላምበርዝ፣ “በዚያን ቀን በምክር ቤቱ የተፈጸመው ጥቃት በአገራችን ባላው የህግ የበላይነት ላይ የተፈጸመ ጥቃት ነው” ማለታቸውም ተዘግቧል፡፡  

Source: Link to the Post

Leave a Reply