You are currently viewing “በምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀውን ኦነግ ሸኔን ታጣቂ ኃይል  «ኢመደበኛ»፥ የሚፈጽመውንም ዘር ተኮር ጅምላ ፍጅት «ግጭት» በማለት ሲገልጹ ይስተዋላሉ።” የተከበሩ ሙሉቀን አሰፋ ከአብን…

“በምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀውን ኦነግ ሸኔን ታጣቂ ኃይል «ኢመደበኛ»፥ የሚፈጽመውንም ዘር ተኮር ጅምላ ፍጅት «ግጭት» በማለት ሲገልጹ ይስተዋላሉ።” የተከበሩ ሙሉቀን አሰፋ ከአብን…

“በምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀውን ኦነግ ሸኔን ታጣቂ ኃይል «ኢመደበኛ»፥ የሚፈጽመውንም ዘር ተኮር ጅምላ ፍጅት «ግጭት» በማለት ሲገልጹ ይስተዋላሉ።” የተከበሩ ሙሉቀን አሰፋ ከአብን በፓርላማ ተገኝተው ለጠ/ሚ አብይ አህመድ ካቀረቧቸው ጥያቄዎች አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የተከበሩ ሙሉቀን አሰፋ ከአብን በፓርላማ ተገኝተው ለጠ/ሚ አብይ አህመድ በርካታ ጥያቄዎችን አንስተዋል። ያቀረቧቸው ጥያቄዎችም:_ 1) ሰላማዊ ሰልፍ መከልከልና አለፍ ሲልም በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ እርምጃ መውሰድ ኢትዮጵያ የገባቻቸውን ዓለም አቀፋዊና አሕጉራዊ ስምምነቶች እንዲሁም በኢፌዴሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 30 ላይ የተቀመጠውን የዜጎች መብት የሚጋፋ ነው። ምን አስተያየት አለዎት? 2) በአማራ ሕዝብ ላይ ባለፉት 31 ዓመታት በተለይም ባለፉት 4 ዓመታት በማያባራ መልኩ እየተፈፀመ ያለው የዘር ፍጅት የኢትዮጵያ የብሔራዊ ደኅንነት ስጋት ነው ብለው ያምናሉ ወይ? የዘር ፍጅቱንስ መንግስትዎ መቼና እንዴት ለማስቆም እያሰበ ነው? እርስዎ የሚመሩት የፍትኅ ተቋም እስከዛሬ ድረስ በዘር ፍጅት ፈፃሚዎች ላይ ለምን ክስ መመስረት አልተቻለውም? በመንግስትዎ በኩል የማይቻል ከሆነ ጉዳዩን ወደ ዓለምአቀፍ ፍርድቤት በመውሰድ የዘር ፍጅት ሰለባዎች ፍትኅ እንዲያገኙ ለማድረግስ ምን ያህል ቁርጠኛ ነዎት? 3) እርስዎ በፕሬዝዳንትነት የሚመሩት ገዥው የብልጽግና ፓርቲ ከትሕነግ ጋር ለመደራደር መወሰኑና ተደራዳሪዎችን መሰየሙንም ሰምተናል። ትሕነግ በአገር አንድነትና የሕዝብ ደኅንነት ላይ የከፈተው ጦርነት አገራዊ ሆኖ እያለ መሰል ጉዳዮችን ገዥው ፓርቲ በብቸኝነት ለመደራደር እንዴት ተነሳ? ማብራሪያ ቢሰጥበት። 4) በተደጋጋሚ ጊዜ አሸባሪው ሸኔ የሚፈጽማቸውን የሽብር ድርጊቶችን ለማውገዝ ዳተኝነት ያሳያሉ ተብለው በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ይታማሉ። ሲቀጥሉም በምክር ቤት ደረጃ አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀውን ኦነግ ሸኔ ታጣቂ ኃይል «ኢመደበኛ»፥ የሚፈጽመውንም ዘር ተኮር ጅምላ ፍጅት «ግጭት» በማለት ሲገልጹ ይስተዋላሉ። ፍትኅ ወንጀሉንና ወንጀለኞችን በስማቸው ከመጥራት ይጀምራልና፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ ለሚቀርብብዎት ወቀሴታ ምላሽዎ ምንድን ነው?

Source: Link to the Post

Leave a Reply