በምዕራባዊው የወሎ ክፍል የነበረውን የወራሪ ኃይል በከባድ መስዋዕትነት ሲጠራርግ የሰነበተው የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ዛሬ ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ደሴ ከተማ መግባቱን…

በምዕራባዊው የወሎ ክፍል የነበረውን የወራሪ ኃይል በከባድ መስዋዕትነት ሲጠራርግ የሰነበተው የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ዛሬ ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ደሴ ከተማ መግባቱን አሰታወቀ። ኅዳር30/2014/አሻራ ሚዳያ/ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዳስታወቀዉ በምዕራባዊው የወሎ ክፍል የነበረውን የወራሪ ኃይል በከባድ መስዋዕትነት ሲጠራርግ የሰነበተው የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ዛሬ ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ደሴ ከተማ ገብቷል። በዚህም በምስራቅ በኩል የነበረውን የጠላት ጦር ድል አድርጎ ደሴ ከገባው የወገን ጦር ጋር ተቀላቅሏል ብሏል ። የሕዝባዊ ኃይሉ ብርጌድ ወደ ደሴ ከተማ ሲገባ የደሴ እና አካባቢዋ ሕዝብ ደማቅ አቀባበል አድርጎለታል ያለ ሲሆን የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ሁሉም የአማራ ግዛቶች ነፃ እስኪሆኑ ድረስ የሚያደርገውን ተጋድሎ የሚቀጥል መሆኑን በድጋሚ ያረጋግጣል ብሏል። ክብር እና ሞገስ ሰማዕትነት ለቀበሉ ጓዶቻችን! አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! ሕዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply