በምዕራብ ሐረርጌ ጭሮ ከተማ በሚገኘው በደብረ ሲና ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ ዝርፊያ መፈጸሙ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 26 ቀን 2015 ዓ/ም…

በምዕራብ ሐረርጌ ጭሮ ከተማ በሚገኘው በደብረ ሲና ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ላይ ዝርፊያ መፈጸሙ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 26 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራብ ሐረርጌ ጭሮ ከተማ በሚገኘው በደብረ ሲና ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ዛሬ የካቲት 25 ቀን 2015 ዓ.ም ኪዳን እናደርሳለን ባሉ ከሕገ ወጡ ተሿሚ ወገን በሆኑ 4 ግለሰቦች አማካኝነት ከቤተ ክርስቲያኑ ሽቶ፣ ዕጣንና መብዓ ይዘው ሲወጡ መያዛቸውን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ ሁኔታውን የተመለከተው የቤተ ክርስቲያኑ ጠባቂ ጥይት በመተኮስ ምእመናን ተሰብስበው ሁለቱ ግለሰቦች ሊያዙ ችለዋል፡፡ ዝርፊያ የፈጸሙት ግለሰቦችን ምእመኑ ለከተማው ፖሊስ ያስረከበ ቢሆንም የከተማው ፖሊስ ግን ግለሰቦቹ ይህንን አያደርጉም አውቃችሁ ነው በሚል ያለምንም ማጣራት ግለሰቦቹን መልቀቁ ተገልጿል፡፡ በአንጻሩ የቤተ ክርስቲያኑን ጠባቂ ለምን ወደ ሰማይ ተኮስክ በሚል ማሰራቸውን ለመረዳት ስለመቻሉ የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply