በምዕራብ ሐረርጌ 220 የተለያዩ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችና የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

በምዕራብ ሐረርጌ 220 የተለያዩ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችና የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ሐረርጌ ሐብሮ ወረዳ 220 የተለያዩ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችና የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ፡፡

ክላሽን ጨምሮ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች፣ ቦምብ እና ሽጉጦች እንዲሁም ከ897 ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን ኦ ቢ ኤን ዘግቧል፡፡

የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሳጂን ተመስገን ከድር ኮንትሮባንድ ሕጋዊ ንግድ ላይ ተጽዕኖ በመፍጠር የሃገር እድገትን እንደሚጎዳ ተናግረዋል፡፡

የሐብሮ ወረዳ ወንጀል ምርመራ ስራ ሂደት ኃላፊ ኢንስፔክተር ኃይለማሪያም ጥበቡ በበኩላቸው፥ ህብረተሰቡ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎችን በመጠቆም እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

 

 

The post በምዕራብ ሐረርጌ 220 የተለያዩ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችና የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply