You are currently viewing “…በምዕራብ ሸዋ ኢሉ ገላን ወረዳ ኦበራ ቀራሩ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር በኦነግ ሸኔ ቁጥጥር ስር ወድቋል! ባህርዳር:- የካቲት 30/2014 ዓ.ም                 አሻራ ሚዲያ እስከ አሁ…

“…በምዕራብ ሸዋ ኢሉ ገላን ወረዳ ኦበራ ቀራሩ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር በኦነግ ሸኔ ቁጥጥር ስር ወድቋል! ባህርዳር:- የካቲት 30/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ እስከ አሁ…

“…በምዕራብ ሸዋ ኢሉ ገላን ወረዳ ኦበራ ቀራሩ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር በኦነግ ሸኔ ቁጥጥር ስር ወድቋል! ባህርዳር:- የካቲት 30/2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ እስከ አሁን የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 5 ሰዎች ተረሽነዋል። 6 የብልፅግና የቀበሌ የካቢኔ አባላት ደግሞ ታፍነው ተወስደዋል። 1ኛ፦ አቶ ታምራት ገበሬ (የብዙዎች አባት የሆኑ፣ ታዋቂ የአጥንት ስብራት ወጌሻ፣ ሰውም ከብትም ሲሰበር የሚጠግኑ የታወቁ እጀ መድኃኒት ተወዳጅ ሃኪም ተረሽነዋል። 2ኛ፦ መብራቱ ታምራት። ልጃቸው ነው። ወይኔ አባቴን ብሎ ሲሄድ አባቱ ሬሳ ላይ ረሽነውታል። አባዬ፣ ወንድሜ ብሎ ያለቀሰው 3ኛው ክንዱ ታምራትም። በአባቱና በወንድሙ አስከሬን ላይ ረሽነውታል። የሟች አባት ወንድም አቶ ተመስገን ገብሬ ወንድሜን ብሎ ከጎረቤት ዘሎ ሲመጣ እሱንም 4ተኛ አድርገው ረሽነውታል። የአባቱን መረሸን ሰምቶ የመጣውን አቶ ሃብቴ ተመስገንንም 5ተኛ አድርገው ረሽነውታል። የአንድ ቤተሰብ አባላት ወንዶቹ በሙሉ ተመርጠው ተረሽነዋል። “…ገዳዮቹ ረሽነው ከሄዱ በኋላ ሲነጋ የመንግሥት የጸጥታ ኃይል ነኝ የሚለው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል መጥቷል። አስከሬኖቹንም ለቅሞ፣ አንድም ቤተሰብ በሌለበት፣ እንዳይገኝ በተደረገበት በእጃጂ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ቀብሮአቸዋል። •…የቀበሌ የብልፅግና የካቢኔ አባላት የሆኑ ግለሰቦች ደግሞ ባይረሸኑም ታፍነው ወደ ጫካ ይዘዋቸው መሄዳቸው ነው የተነገረው። 1፥ ኦቦ ቱሉ በቀለ 45 10ል 2፥ አቶ ገዝሙ ቢራራ 60/8 3፥ ኦቦ ቶሎሳ ዳዲ 4፥ አቶ ግርማ ዘነበ 5፥ ኦቦ ግርማ ሳቀታ 6፥ ኦቦ ደጀረጄ ጢቆ እና ለጊዜው ስማቸው ያልተገለፁ ሰዎች ታፍነው ተወስደዋል። “… በአጠቃላይ በአስፋልት ላይ ያሉ ከተሞች ሲቀሩ በሙሉ የምዕራብ ኦሮሚያ በኦነግ ሸኔ አስተዳደር ተተክቷል። ሆበራ ቀራሩ፣ ረሶሶ ቃሚኖ፣ ጎተራ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ዲቢ፣ ሰዮ እና ዳኖ ወረዳ፣ ካራ፣ ሳቻ በሙሉ በኦነግ ሸኔ ቁጥጥር ስር ወድቋል። “…ደወዬ ያገኘሁአቸው ሰዎች በሙሉ በዚህ ውድቅት ሌሊት ከተማውን ጥለው ጫካ ሆነው ነው ያወሩኝ። ከወር በፊት ደውለው 200 ሺ ብር አዘጋጅ ይሉሃል። የአንተ ስራ አዘጋጅተህ መጠበቅ ነው። ለፖሊስ ስታመለክት” ፖሊሱ አዘጋጅ ካሉህ አዘጋጅ፣ መኖር አትፈልግም? እንዴ? ይልሃል። ወር ሲደርስ ድንገት ይመጣሉ። ብሩን በ10 ደቂቃ ውስጥ ከቤትህ ደጃፍ አስቀምጥ ይሉሃል። ካስቀመጥክ ብሩን አንስተው ሳይነኩህ ያልፋሉ። ከሌለህ ግን እዚያ ቤት ውስጥ ያለውን ሰው በሙሉ ይረሽናሉ። ኦሮሞ ነኝ ብትል እንኳ እስከ ቅድመአያትህ ይቆጥራሉ። በዚያ ኦሮሞ ቢያጡ የእናትህን ዘር ይቆጥራሉ። በመሃል የዐማራ ስም ካገኙ ይረሽኑሃል። መመሪያው እንደዚያ ነው ነው የሚሉት። “…የኦነግ ሸኔ አዛዥ ናቸው፣ መመሪያና ስምሪት የሚሰጡ ናቸው የተባሉ 3 ሰዎች ስልክ ተሰጥቶኝ ደውዬ ነበር። ሁለቱ አንስተው አውርተውኛል። ክፈል የተባልከውን ክፈል ነው ያሉኝ። የሚገርመው የ3ቱም ስልክ ማታ ማታ ለስምሪት ሲወጡ ነው አክቲቭ የሚሆነው። “…በጫካ ያሉትን አይዟችሁ አልኳቸው። የጸጥታ ኃይሎች ምንም አይረዷችሁም ወይ ብያቸውም ነበር። የአካባቢው የጸጥታ ኃይል ኦነግሸኔ ማታ የሚገባ ከሆነ ቀን ከተማውን፣ ቀበሌውን ለቆ ይወጣል። እነሱ መታ እየተኮሱ ይገባሉ። ከገቡ በኋላ በያዙት ሊስት መሰረት የሚረሸነውን ረሽነው። የሚዘረፈውን ዘርፈው ይመለሳሉ። ጠዋት ፖሊስ ይመጣል። አስከሬን አንሥቶ ይቀብራል። አብረው ነው የሚሠሩት። “…አንዳንዴ ግን አንዳንዴ የፌደራል ፖሊሶች፣ የኦሮሚያ ፖሊስና የመከላከያም ወታደሮች ይመጣሉ። አካባቢውን የማያውቁ፣ አብዛኛው ዐማሮችና የደቡብ ልጆች፣ እንዲሁም ኦሮሞ ሆነው ኦርቶዶክስ የሆኑት ተልከው ይመጣሉ። የአካባቢው የጸጥታ ኃይል ከኦነጎቹ ጋር አብሮ ስለሚሠራ የተሳሳተ መረጃ ሰጥቶ እንዳለ በደፈጣ የስጨርሳቸዋል። በሙሉ የሚያልቁት በዚህ መንገድ ነው። ደግሞ ትናንሽ ልጆች እኮ ናቸው። መጪው ጊዜ ከባድ ነው። ዘመድኩን በቀለ ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply