You are currently viewing በምዕራብ ሸዋ ዞን የባኮ ትቤ ወረዳ እና የምስራቅ ወለጋ ዞን የጉበሰዮ ወረዳ የአማራው ማህበረሰብ አሁንም የድረሱልን ጥሪ ነው እያሰማ ነው።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ህዳር 1 ቀን 20…

በምዕራብ ሸዋ ዞን የባኮ ትቤ ወረዳ እና የምስራቅ ወለጋ ዞን የጉበሰዮ ወረዳ የአማራው ማህበረሰብ አሁንም የድረሱልን ጥሪ ነው እያሰማ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 1 ቀን 20…

በምዕራብ ሸዋ ዞን የባኮ ትቤ ወረዳ እና የምስራቅ ወለጋ ዞን የጉበሰዮ ወረዳ የአማራው ማህበረሰብ አሁንም የድረሱልን ጥሪ ነው እያሰማ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 1 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሸቦካ በተባለ ቦታ አማራዎችን እየገደሉም እያገቱም ወስደዋል ያሉት የአካባቢው ነዋሪወች የማያባራው የአማራ የደም ዝናብ በወለጋና በባኮ ትቤ ወረዳ ዛሬም እንደዚህ ቀደሙ እየፈሰሰ ነው። አማራን የኔ ማህበረሰብ ነው የሚለው የለም ወይ? ሲሉ ነዋሪዎች በሲቃ ድምጽ በምሬት እያለቀሱ ጠይቀዋል። በምስራቅ ወለጋ ዞን በጉበሰዮ ወረዳ ሸቦካ በሚባለው አከባቢ ሁለት ንፁሐን አማራዎችን በማገት ሁለት ንፁሐንን አግተው ወስደዋል። እንደዚህ በተጠና ጥቃት አንድ ሁለት እያልን አለቅ:: እባካችሁ አሁንም ለቀረነው ድረሱልን ሲሉ ተማፅነው።፥ የምዕራብ ሸዋ ዞን የባኮትቤ ወረዳ የምስራቅ ወለጋ ዞን አጎራባች በመሆናችን በተጠናው ጥቃት ሰለባ እየሆንን ነው። የኦነግ ሸኔ አሸባሪው ቡድን እስከ አፍንጫው የታጠቀ፣ የተደራጀ ቡድን ነው። በዚህም የተነሳ የሸኔ ሐይልን ለመፋለም የምንጠራው እኛ የገበሬ ሚኒሾች ነን። የመንግስት ሐይል እስካሁን የለም፤ አልደረሰልንም ብለዋል:: አጠቃላይ የምስራቅ ወለጋ ዞን ስር የሚገኙ ወረዳዎች እና የገጠር ቀበሌዎች የኦነግ ሸኔ ቦታዎች ናቸው። ከእነዚህ መካከል ደግሞ፦ 1- በሲቡ ስሬ ወረዳ፥ አርብ ገበያ፣ ሸበካ፣ ለገኢያ ቀበሌና ሌሎችም የወረዳው ቀበሌዎች በኦነግ ሸኔ ቁጥጥር ስር ናቸው። በእነዚህ ቀበሌዎች የአማራ ማህበረሰብ አጠቃላይ ወጥቷል። የቀረውም በሸኔ ሰይፍ ሰለባ ሆኗል። 2- በጎቡሰዮ ወረዳም የመንግስት እርሻ ልማት ተዘርፏል። መሠረተ ልማት ወድመዋል። የመንግስት መዋቅር ፈርሶ የኦነግ ሸኔ አደረጃጀት የተመሠረተባቸው አከባቢዎች ሆነዋል። ከየአካባቢዎቹ ተፈናቅለው ወደ ወረዳው ከተማ በአኖ ከተማ የተጠለሉትም ቀናቸውን በመጠባበቅ ላይ ናቸው። በመጨረሻም በአራቱም አቅጣጫ ተከቦ የከረመው የባኮ ትቤ ወረዳ ነዋሪዎች ዛሬ ነብስ ውጭ ነብስ ግቢ ላይ ነን። እባካችሁ እኛ የገበሬ ሚኒሾች በወረዳው አስተዳደር ውጡ?! ከኦነግ ጋር ግጠሙ!? አለበለዚያ ወደከተማዋ መግባታቸው አይቀርም!? በማለት መንግስት ባለበት ሐገር ለማገዶነት በአነስተኛ የሚኒሻ አደረጃጀት ሊያስፈጁን ነው⁈ ድረሱልን! ሲሉ ተማፅነዋል ሲል ንስር ብሮድካስት ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply