You are currently viewing በምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ በአማራዎች ላይ የሚፈጸመው የተደራጀ ግፍ እንደቀጠለ ነው ተባለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ. ም         አዲስ አበባ ሸዋ በም…

በምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ በአማራዎች ላይ የሚፈጸመው የተደራጀ ግፍ እንደቀጠለ ነው ተባለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ. ም አዲስ አበባ ሸዋ በም…

በምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ በአማራዎች ላይ የሚፈጸመው የተደራጀ ግፍ እንደቀጠለ ነው ተባለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ. ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ ከግድያውና ዝርፊያው በተጨማሪ በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ አማራዎች በማንነታቸው ምክንያት በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በመንግስት መዋቅር ውስጥ በተሰገሰጉ የጥፋት ተባባሪዎቹ የተፈናቀሉ መሆኑ ይታወቃል። በቅርቡ በአዲስ አበባ ለሚኩራ ክ/ከተማ 1,500 በላይ የሚሆኑ ከዳኖ የተፈናቀሉ አማራዎች ስብሰባ በማስፈቀድ መወያየታቸው ተገልጧል። በመድረኩም ከ500 በላይ አማራዎች ተገኝተው 20 አባላት ያሉት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አደራጅተው ለተለያዩ ተቋማት የደረሰባቸውን በደል በዝርዝር በማሳወቅ ፍትህ እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ላይ ናቸው። ከጥቅምት ወር መግቢያ ጀምሮ እንደ አዲስ አማራውን የማፈን፣ የማሳደድና የመግደል የወንጀል ድርጊት ተጠናክሮ መቀጠሉ ተሰምቷል። ከሰሞኑ እንኳ 3 አማራዎች ተለይተው ከተሳፈሩበት መኪና እንዲወርዱ በማድረግ በግፍ መገደላቸውን ከሟች ቤተሰብ የተገኘ መረጃ ያመለክታል። አማራ እንዳይወጣ፣ አሳፍሮ የተገኘ ሰው ይቀጣል በማለት እያሳደዱ ነው፤ እቅዳቸው አማራውን ለመጨፍጨፍ በመሆኑ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ብለዋል። መንግስት ካለ በአስቸኳይ የጸጥታ አካል መድቦ ከእልቂት ሊታደገን ይገባል ብለዋል። ፎቶ:_ፋይል

Source: Link to the Post

Leave a Reply