በምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ቡድን በተደጋጋሚ ተኩስ እየከፈተ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 8 ቀን 2015 ዓ/ም…

በምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ቡድን በተደጋጋሚ ተኩስ እየከፈተ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 8 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ቡድን በተደጋጋሚ ተኩስ እየከፈተ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የገለጹት ነዋሪዎች ህዳር 7/2015 ከሌሊት ጀምሮ በዳኖ ሮቢት ከተማ እና በጉልፋ ቀበሌ የወረራ ሙከራ አድርጓል። በዳኖ ሮቢት ተኩስ ከፍቶ ወረራው ያልተሳካለት የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን በተመሳሳይ በጉልፋ ቀበሌ ለሰዓታት የቆዬ ተኩስ ከፍቶ እንደነበር ተገልጧል። በጉልፋ ከሌሊት ጀምሮ እስከ ህዳር 8/2015 ከቀኑ 5 ሰዓት ተኩስ ከፍቶ ቢቆይም በአካባቢው ያሉ ሚሊሾችና አርሶ አደሮቸፈ ባደረጉት የአልሞት ባይ ተጋድሎ ወረራው ሳይሳካለት ወደ ጫካ ተመልሷል። በጥቃቱም አንድ ሚሊሻ ሲገደል፣ ሌሎች 2 ሚሊሾችን ያቆሰለው ቡድኑ፣ በራሱም በኩል ሰዋዊ እና ቁሳዊ ውድመት የደረሰበት መሆኑ ተገልጧል። አሁን ላይ ከ5 ሽህ በላይ የሰው ኃይል በማሰማራት ከምስራቅ ወለጋ ዞን ተነስቶ ወረራ ሊፈጽም ስለመሆኑ መረጃ የደረሳቸው ነዋሪዎች መንግስት ተጨማሪ ኃይል እንዲልክላቸው ጥሪ አድርገዋል። በምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳን ጨምሮ ኖኖ፣ ጅባትና አዋሳኙ አመያ አካባቢዎች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በተባባሪዎቹ ተደጋጋሚ ጥቃት የደረሰባቸው በመሆኑ በሽህ የሚቆጠሩት አማራዎች ተፈናቅለው በከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸው ይታወቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply