You are currently viewing በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት እራሱን “የኦሮሚያና የብሔር ብሔረሰቦች ሲኖዶስ” በሚል የሚጠራው ሕገወጥ የነውጠኞች ስብስብ የወንብድና ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠሉን የሻሸመኔ ምዕመናን ገለፁ። የ…

በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት እራሱን “የኦሮሚያና የብሔር ብሔረሰቦች ሲኖዶስ” በሚል የሚጠራው ሕገወጥ የነውጠኞች ስብስብ የወንብድና ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠሉን የሻሸመኔ ምዕመናን ገለፁ። የ…

በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት እራሱን “የኦሮሚያና የብሔር ብሔረሰቦች ሲኖዶስ” በሚል የሚጠራው ሕገወጥ የነውጠኞች ስብስብ የወንብድና ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠሉን የሻሸመኔ ምዕመናን ገለፁ። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 11/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት እራሱን “የኦሮሚያና የብሔር ብሔረሶቦች ሲኖዶስ” በሚል የተደራጀው ሕገ ወጥ የነውጠኞች ስብስብ በሻሸመኔ ከተማ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አድባራት ላይ የወረራ እና የዝርፊያ የውንብድና ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠሉን በሻሸመኔ የሚገኙ ምዕመናን ለተሚማ ገልፀዋል። ትናንት ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም እኒህ ነውጠኛና በውንብድና የተሰማሩ አካላት መሳሪያ በታጠቁ አካላት ታጅበው በሻሸመኔ ደብረ አስቦ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን በመግባት መደበኛ አገልጋዮች ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ እንደፈፀሙና እንዲሁም ነገ ግንቦት 12 በሚከበረው ዓመታዊ የጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የንግሥ በዓል ላይ ተገኝተን አገልግሎት እንሰጣለን በሚል ለደብሩ ደብዳቤ እንዳስገቡና በእለቱም ለዘረፋ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እንደሚመጡ ተገልጿል። የሻሸመኔ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን እና የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊዎች የዚህን ሕገ ወጥ ወረራ እና ዝርፊያ ለማስቆም ፍቃደኛ እንዳልሁኑ በሻሸመኔ የሚገኙ ምንጮች ገልፀዋል። በሻሸመኔ ከተማ የሚገኙ ምዕመናን በበዓሉ ቀን በቤተ ክርስቲያን በመገኘት ቤተ ክርስቲያኑን በንቃት እንዲጠብቅ እና በዕለቱ ምንም አይነት የገንዘብ መሰብሰብ መርሐግብር እንዳይደረግ ምዕመናንንም ወቅታዊ ችግሩን ከምት በማስገባት የስጦታ እጃቸውን እንዲሰበስቡ እናሳስባለን ሲል የሻሸመኔ ከተማ ኦርቶዶክሳውያን ሕብረትም አስታውቋል። ተሚማ እንየዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply