በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት 5 ሰላማዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በግፍ መገደላቸው ተገለጸ። የአማራ ሚዲያ ማእከል ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ በምዕራ…

በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት 5 ሰላማዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በግፍ መገደላቸው ተገለጸ። የአማራ ሚዲያ ማእከል ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሄበን አርሲ ወረዳ 5 ኦርቶዶክሳውያን ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ማለዳ ላይ በህገወጥ ታጣቂዎች መገደላቸውን የወረዳ ቤተ ክህነቱ ሕዝብ ግንኙነት አስታወቀ። ሀገር ሰላም ብለው ወደዕለት ተግባራቸው በመሰማራት ላይ እንዳሉ አጥቂዎቹ ታጣቂዎች ክርስቲያኖቹን በስም እየጠሩ በግፍ በአደባባይ ገድለዋቸዋል ሲል የወረዳ ቤተ ክህነቱ ሕዝብ ግንኙነት አክሎ ገልጿል። በአከባቢው ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት በአከባቢው ሥጋት ሆነው የቆዩ ሲሆን ከሰኔ 23ቱ 2012 ዓ.ም ጥቃት በኋላ በርከት ያሉ ክርስቲያኖች ላይ ጥቃት ሲደርስ ያሁኑ ከፍተኛ መሆኑ ታውቋል። በጥቃቱ ሰለባ የሆኑ 5ቱም ክርስቲያኖች በደጋጋ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በትናንትናው ዕለት ጸሎተ ፍትሃት ተደርጎላቸው የወረዳ ቤተክህነቱ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ሥርዓተ ቀብራቸው መፈጸሙ ታውቋል። የአከባቢው ነዋሪዎችም ደህንነታቸው በሰላም ተጠብቆ እንዲኖር መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ጥበቃ እንዲያደርግላቸው መጠየቃቸውም ገልጾለ ቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጆቻቸው መጽናናትን ተመኝቷል። ዘገባው የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት ሕዝብ ግንኙነት ነው ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply