
በምዕራብ አርሲ እና በምዕራብ ሐረርጌ አህጉረ ስብከት እየተደረገ ያለው ማሳደድና እሥር እንደቀጠለ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ሕገ ወጡ ቡድን ካሳለፍነው እሑድ ጀምሮ የሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን መውረሩና አገልግሎት እንዲጀመር አገልጋዮቹን እያስገደዱ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል። ከዚያም ባለፈ የደብሩ አስተዳዳሪ የነበሩት አባ ተስፋ ጊዮርጊስ የተባሉት ግለሰብ ለምን ከሕገ ወጡ ቡድን ጋር ይሠራሉ ብለው የጠየቋቸውን 8 ወጣቶችን አሳስረዋል። ከዚያ በተጨማሪ ከሥር በፎቶ ላይ የሚታዩት ግለሰቦች ሕገ ወጡን ቡድን በመደገፍና ወጣቶችን በማሳሰር ላይ ይገኛሉ። በመጀመሪያው ፎቶ ላይ የሚታየው ግለሰብ አቶ አቢቲ ይባላል። ይህ ግለሰብ:_ 1) የዛሬ ወር ጥር 27/2015 ዓ.ም በሻሸመኔ በነበረው ጭፍጨፋ ላይ ሕገ ወጦቹን ደግፎ ሲመራ ሲያስተባብር የነበረ፣ 2) የማኅበረ ቅዱሳንን አባላትና የሰንበት ት/ቤቱን አገልጋዮችን በግቢው ውስጥ እየጠቆመ ሲያስጨፈጭፍ የነበረ፣ 3) ከጭፍጨፋው ማግስት እሑድ ጥር 28/2015 ዓ.ም ሕገ ወጦቹ በቅዱስ ሚካኤል ተገኝተው ፎቶ ሲነሱ በነበረበት ወቅት ፎቶ ሲያነሳና በመኪናው እያጀበ ሲመራ የነበረ ግለሰብ ነው። 4) ይህ ግለሰብ የ”አባ ገብረ እግዚአብሔር ታደለ” (የሕገ ወጡ ጳጳስ) የፋይናንስ ጉዳዮች አስፈጻሚ ከመሆኑም ባለፈ ቅድስት ቤተክርስቲያን አንክድም ያሉ ታማኝ የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህናትና ዲያቆናትን “ገብታቹ የምናዛችሁን ብትፈፅሙ ይሻላችኋል አለበለዚያ በፖሊስ ማንቁርታቹ ተይዞ ትገቧታለችሁ” በማለት እስከ ማስፈራራት ደርሷል። 5) ይህንን ነውረኛ ተግባሩን የሚቃወሙ ምእመናንን በማሳፈስ እና በማሳሰር ላይ ይገኛል። ሁለተኛው የደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ቀሲስ አሳዬ ይባላሉ። 1) እኚህ ግለሰብ ከአባ ተስፋ ጊዮርጊስ ጋር በመመሳጠር የሕገ ወጡን አካል ጉዳይ እያስጸሙ ይገኛሉ። 2) ከውጪ በመሆን ወጣቶችን እየጠቆሙ በማሳሰር፣ እንዲሁም የወንጀላቸው ተባባሪ አንሆንም የሚሉ ካህናትን ለፖሊስ በመጠቆም እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። በተያያዘ ዜና በምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጭሮ ከተማ በምዕራብ ሐረርጌ በጭሮ ከተማ የቤተ ክርስቲያን ልጆችን እያሳደዱ ማሰሩ እንደቀጠለ መሆኑን ሀገረ ስብከቱ ገልጿል። በትናንትናው ዕለት የካቲት 27/2015 ዓ.ም አቶ ሄርሞን ከበደ የተባሉ ኦርቶዶክሳዊ እንደታሰሩና ሌሎች ወጣቶችም እየታደኑ እንደሆነ ተገልጿል ሲል ተዋህዶ ሚዲያ አጋርቷል።
Source: Link to the Post