በምዕራብ እና ማዕከላዊ አፍሪካ 55 ሚሊዮን ዜጎች ለረሃብ ተጋጠዋል ተባለ።የዋጋ ግሽበት እና የሀገር ውስጥ የምርት መቀነስ ለዜጎች የርሃብ ቀውስ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል።በዚህም ምክንያት 5…

በምዕራብ እና ማዕከላዊ አፍሪካ 55 ሚሊዮን ዜጎች ለረሃብ ተጋጠዋል ተባለ

የዋጋ ግሽበት እና የሀገር ውስጥ የምርት መቀነስ ለዜጎች የርሃብ ቀውስ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል።

በዚህም ምክንያት 55 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች በሚቀጥሉት ወራት እራሳቸውን ለመመገብ እንደሚቸገሩ የተባበሩት መንግስታት ድርጀት አስጠንቅቋል።

ከሰኔ እስከ ነሃሴ ባለው ጊዜ ለርሃብ  የሚጋለጡ ዜጎች ቁጥር በአራት እጥፍ መጨመሩን፣ የዓለም የምግብ ፕሮግራም፣ የምግብና እርሻ ድርጅት እንዲሁም ዩኒሲኤፍ በጋራ በሰጡት መግለጫ ላይ ተመላክቷል።

ናይጄሪያ፣ጋና፣ ሴራሊዮን  እና ማሊ በርሃብ ቀውሱ በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ መሆናቸው ተጠቁሟል።

በአምስት ዓመት ውስጥ ያለው የእህል እና ጥራጥሬ ዋጋ ከ10 በመቶ ወደ ከመቶ በላይ በማካኝ ጭማሪ ማሳየቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልጿል።

ድርጅቱ እንደገለጸው፤ ከ10 ህፃናት 8ቱ ከ6 እስክ 23 ወራት ውስጥ ለጤናማ እድገት የሚያስፈልጋቸውን ምግብ እንደማያገኙ ነው።

ከ5 ዓመት በታች ያሉ 16.7 ሚሊዮን  ህፃናት ለተመጣጠነ የምግብ እጥረት እንደሚጋለጡም ተጠቂሟል።

እንዲሁም ከሶስቱ ሁለቱ አባዎራዎች ጤናማ የምግብ ስርዓትን አይከተሉም ተብሏል ።

በእሌኒ ግዛቸው

ሚያዝያ 05 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply