በምዕራብ ወለጋ በንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈፀመው ግድያ

https://gdb.voanews.com/88B76004-B253-4D58-A394-4404FB3CA31A_w800_h450.jpg

በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ውስጥ “የኦሮሞ ነፃነት ሸማቂዎች ወይም ኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በፈፀሙት ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ቁጥራቸው በወል ያልታወቀ ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን ከጥቃቱ ያመለጡ የአይን እማኞች ተናግረዋል።

ማንነትን መሰረት ባደረገው ጥቃት ማዘናቸውን የገለፁት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግሥት ሁሉንም ዓይነት አማራጮች ተጠቅሞ የችግሩን ይነቅለዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ጠላቶች ወይ እኛ እንገዛለን ወይ ሀገር አትኖርም ብለው ተነስተዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለዋል።

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ በወጡት መግለጫ በኦነግ ሸኔ እና በወያኔ የጥፋትና የሽብር ሴራ ኢትዮጵያ አትፈረስም” ብለዋል።

በጥቃቱ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ግን በመንግሥት በወጡ መግለጫዎች አልተጠቀሰም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply