በምዕራብ ወለጋ ዞን በባቦ ወረዳ የሚኖሩ አማራዎች መንግስት የመከላከያ ሰራዊት በማስገባት ከጥቃትና ከስጋት እንዲታደጋቸው ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓም…

በምዕራብ ወለጋ ዞን በባቦ ወረዳ የሚኖሩ አማራዎች መንግስት የመከላከያ ሰራዊት በማስገባት ከጥቃትና ከስጋት እንዲታደጋቸው ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓም…

በምዕራብ ወለጋ ዞን በባቦ ወረዳ የሚኖሩ አማራዎች መንግስት የመከላከያ ሰራዊት በማስገባት ከጥቃትና ከስጋት እንዲታደጋቸው ጠየቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ አካባቢ ስብሰባ ላይ በነበሩ አማራዎች ላይ በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የተፈፀመው አሰቃቂ የጅምላ ፍጅት የሚረሳ አይደለም። ታጣቂዎቹ በምዕራብ ወለጋ ዞን በባቦ ወረዳም ተመሳሳይ ማንነት ተኮር ወንጀል ለመፈፀም በተለያየ ጊዜ እየዛቱ በመሆኑና ከሰሞኑም እያደረጉት ያለውን እንቅስቃሴ በስጋት እንዲመለከቱት ስለማድረጉ ነዋሪዎች ገልፀዋል። ከባቦ ወረዳ ያነጋገርናቸው ነዋሪ እንደሚሉት ዛሬ ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በአንቡላንስ ተሳፍረው ከቦኒ ወደ ነጆ ሲጓዙ የነበሩ ወላዶችን በማስወረድ ተሽከርካሪውን ስለማቃጠላቸው ተናግረዋል። ወላዶች ስላሉበት ሁኔታም መረጃ የለንም ነው ብለዋል። በተጨማሪም ከ50 በላይ ቁጥር ያላቸው የቡድን መሳሪያ የታጠቁ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከባቦ ወረዳ ወደ ቦኒ ቀበሌ በመለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ሲጓዙ መንገድ ላይ በማስወረድ ከፍተኛ ፍተሻ ስለማድረጋቸው ተገልጧል። በተመሳሳይ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በባቦ ወረዳ ኮንፈር ወደተባለ ቀበሌ በማቅናት አካባቢውን ስለመቆጣጠራቸው የነገሩን ነዋሪው ለታጣቂዎች ስንቅና ትጥቅ የሚያቀብል ስለመኖሩ ተናግረዋል። የኦሮሚያ ልዩ ሀይልም ኦነግ ሸኔ በአማራ ላይ የፈለገ ወንጀል ቢፈፅም እንኳ ጨክኖ እርምጃ የሚወስድበት ሁኔታ የለም ያሉት ምንጫችን በአካባቢው ላይ ያለውን የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችን አካሄድ ተረድቶ ቀድሞ መዋቅሩን በመፈተሽ እና የመከላከያ ሰራዊትን በማስፈር እንዲታደጋቸው ጥሪ አድርገዋል። በድምፅ የተደገፈውን ሙሉ ዝግጅት በአሚማ የዩቱብ አድራሻ የምናጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply