በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ወረዳ ቦኒ ቀበሌ ከ60 ሺህ በላይ አማሮች ተፈናቅለው ጫካ ላይ መሆናቸዉን እና ለከፋ ችግር መጋለጣቸዉን ተናገሩ ፡፡ ህዳር 10/2014/አሻራ ሚዲያ / በአሸባሪዉ…

በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ወረዳ ቦኒ ቀበሌ ከ60 ሺህ በላይ አማሮች ተፈናቅለው ጫካ ላይ መሆናቸዉን እና ለከፋ ችግር መጋለጣቸዉን ተናገሩ ፡፡ ህዳር 10/2014/አሻራ ሚዲያ / በአሸባሪዉ ኦነግ ሸኔ አሁንም በምዕራብና በምስራቅ ወለጋ ከ90 ሺ በላይ አማሮች ከበባ ላይ ናቸው መንገድ ተዘግቷል ምግብ የለም የሚጠጣ የለም ጎዳና ወድቀዋል ለተጨማሪ ዕልቂት ተከበዋል ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ተረሽነዋል ሃብት ንብረታቸው ተዘርፏል ፡፡ በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ወረዳ ቦኒ ቀበሌ ከ60 ሺህ በላይ አማሮች ተፈናቅለው ጫካ ላይ መሆናቸዉን እና ለከፋ ችግር መጋለጣቸዉን ለአሻራ ሚዲያ በስልክ ተናግረዋል አሁን ላይ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ከኦነግ ጋር አብሮ ሲገድልና ሲዘርፍ ነው የዋለዉ ብለዋል። የቦኒ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አያሌዉ በበኩላቸዉ ከ60 ሽህ በላይ ህዝብ እነደተፈናቀለ ገልፀዉ አሸባሪዉ ኦነግ ሸኔ በከባድ መሳሪያ በመታገዝ ንፁሃንን እየገደለ ነዉ በጣም አደጋ ላይ ነን ብለዋል ለዞን እና ለፌደራል አመራሮችም ብንጠይቅ ሰሚ አላገኘነም ነዉ ያሉት።

Source: Link to the Post

Leave a Reply