በምዕራብ ወለጋ ዞን እና አሶሳ ዞን አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ውጊያ መቀስቀሱ ተገለፀ! ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በሰሞኑ በርካታ የወለጋና የቤኒሻንጉል…

በምዕራብ ወለጋ ዞን እና አሶሳ ዞን አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ ውጊያ መቀስቀሱ ተገለፀ! ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በሰሞኑ በርካታ የወለጋና የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አዋሳኝ አከባቢ ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት በርካታ ከተሞችን ኦነግ ሸኔ ተቆጣጥሯል። በዚህም መሠረት፦ ከአሶሳ- ነቀምት ከነቀምት- ጊምቢ ከጊምቢ- ነጆ ከጊምቢ- ደንቢደሎ ከነጆ- ቤጊ ከቤጊ- አሶሳ እንዲሁም ** ከጉትን- ነቀምት እና እስከ ሐሮ ድረስ መንገዱ ዝግ በመሆኑ የሚመለከታቸው የመንግስት አካል በአስቸኳይ የመፍትሔ አካል እንዲሆኑ ኗሪዎች ጥሪ አቅርበዋል‼ ከሰሞኑ ከተለያዩ የወለጋ ዞኖችና ወረዳዎች እንዲሁም ከተሞች ወደተመደቡበት የዩኒቨርስቲ ምድቦች በየአከባቢው በሚገኙ ሚኒሾች እጀባ የተሸኑ ተማሪዎች በተጠቀሱት አከባቢዎች መንገድ ዝግ በመሆናቸው ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ ተገልጿል። ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ዉስጥ በአሶሳ ዞን የባምባሲ ወረዳ አስተዳደር በወረዳዉ ከምሽት እስከ ንጋት የሚዘልቅ የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን መዘገባችን ይታወሳል። በቤንሻንጉል አሶሳ ከትናንት ጀምሮ በፀናዉ ደንብ መሰረት የመንቀሳቀስ ልዩ ፈቃድ ከተሰጣቸዉ ወገኖች በስተቀር ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ማለዳዉ 12 ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ አይቻልም። የሰዓት ዕላፊው መጣል ምክንያት ደግሞ የባምቢሲን ወረዳ በሚያዋስነዉ በምዕራብ ወለጋ ዞን በተለይም ማናስቡ በተባለ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እና የጉምዝ ታጣቂዎች በከፈቱት ከፍተኛ ውጊያ መሆኑን የአካባቢዉ ነዋሪዎች እና ባለሥልጣናት አስታዉቀዋል። የወረዳ አስተዳደሩ የሰዓት እላፊ ገደብ የጣለዉ ዉጊያ ከሚደረግበት አጎራባች ወረዳ ታጣቂዎች ሰርገዉ እንዳይገቡ ለመቆጣጠር በማሰብ እንደሆነ መግለፁ ይታወቃል። እንደምንጮች ገለፃ ደግሞ የተከፈተውን ተኩስ ለመቀልበስ ከትናንት ጀምሮ እስከ ዛሬ ጸጥታ ኃይሉና ታጣቂዎች እየተዋጉ ነዉ። በጉዳዩ ዙሪያ የተለያዩ እርምጃዎች እየወሰዱ ነው ያሉት የአካባቢው የመንግስት ባለስልጣናት ከትናንት ጀምሮ ሀይሎቻችን ተኩስ ላይ ናቸው፡፡ ሲመሽ ጋብ ብሎ ሲነጋ ውጊያው ይቀጥላል። ከተማ ውስጥም ተኩስ አለ ሲሉ የመንግስት ባለስልጣናት ተናግረዋል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply