በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ኦነግ ሸኔ በአማራ ላይ የፈፀመው አሳዛኝና አሳፋሪ ጥቃት ከትናንት የቀጠለ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው ሲሉ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ሊቀመንበ…

በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ኦነግ ሸኔ በአማራ ላይ የፈፀመው አሳዛኝና አሳፋሪ ጥቃት ከትናንት የቀጠለ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው ሲሉ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ሊቀመንበ…

በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ኦነግ ሸኔ በአማራ ላይ የፈፀመው አሳዛኝና አሳፋሪ ጥቃት ከትናንት የቀጠለ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው ሲሉ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ሊቀመንበሩ አቶ ማሙሸት አማረ ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ሚዲያ ማዕከል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ሊቀመንበር ከሆኑት ከአቶ ማሙሸት አማረ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ቆይታ አድርገናል። አቶ ማሙሸት አማረ በአማራ ህዝብ ላይ በተለያዩ ጊዜያትና አካባቢዎች በአማራ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈፀመ መሆኑ ሁሉም የሚያውቀው የአደባባይ ሚስጥር መሆኑን ገልፀዋል። ይህ ማንነትን መሰረት አድርጎ የሚፈፀመው ጥቃትም ህጋዊ መሰረት፣መዋቅርና አደረጃጀት ተፈጥሮለት ላለፉት 30 ዓመታት ሲተገበር የቆየና አሁንም እንደቀጠለ ነው ብለዋል። ህወሀት በጫካ ማኒፌስቶው አርቅቆና አፅድቆ በአማራና በሌሎችም ላይ ዘግናኝ የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እየፈፀመ እና እያስፈፀመ መቆየቱና አሁንም ስለመቀጠሉ ነው አቶ ማሙሸት የገለፁት። ከሰሞኑ በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ኦነግ ሸኔና ተባባሪዎቹ በአማራ ላይ የፈፀሙት አሳዛኝና አሳፋሪ ጥቃት ከትናንት የቀጠለ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው ሲሉ ነው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ሊቀመንበር አቶ ማሙሸት የተናገሩት። በየዘመናቱ ችግር በደረሰባቸው ጊዜ ሁሉ ከጎናቸው ሆኖ የታደጋቸው የአማራ ህዝብ ዛሬ ላይ ጊዜና ወቅት ሰጠን ብለው ሲያጠፉትና መከራ ሲያይ በዝምታ ከማየት ይልቅ በጋራ በመመከት በኩል መላው ኢትዮጵያዊ የድርሻውን መወጣት አለበት ያሉት አቶ ማሙሸት የአማራ ህዝብም ሁሌም አስከሬን ከመቀበል በመውጣት ተፈጥሮአዊ የሆነ የመከላከል መብቱን መጠቀም አለበት ሲሉ አክለዋል። የአማራን ህዝብ አንገቱን አስደፍተው፣ የስነ ልቦና ቀውስ ውስጥ በመክተት ወይም የዘር ማጥፋት ወንጀልን በመፈፀም አገርን ለማፍረስ በማሰብ የሚያደርጉት የሴራ መንገድ ከቶውም አይሳካላቸውም፤ አማራንም ሆነ የኢትዮጵያን ህዝብ ካለማወቅ የሚደረግ ከንቱ እንቅስቃሴ ነው ብለዋል። መንግስት ቀዳሚ የሆነውን የህዝብን ሰላምና ደህንነት የማስከበር ኃላፊነቱን ይወጣ ማለቱ ሰልችቶናል ያሉት አቶ ማሙሸት ህዝብ በጎበዝ አለቃ ተደራጅቶ ራሱን፣ቤተሰቡን ብሎም አካባቢውን መመከት፣መከላከልና መጠበቅ አለበት ነው ያሉት። በተያያዘ ህወሀት በመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈፀመውን ጭፍጨፋ አሳዛኝ የክህደት ወንጀል መሆኑን የገለፁት አቶ ማሙሸት በመንግስት በኩል የተጀመረው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ አሳስበዋል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ የትግራይን ህዝብ ጨምሮ በህወሀት ላይ የሚወሰደውን እርምጃ መደገፍ አለበት ነው ያሉት አቶ ማሙሸት። ከአቶ ማሙሸት አማረ ጋር የተደረገውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ላይ መከታተል ይችላሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply