You are currently viewing በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ዳግም ወረራ እና ጥቃት ሊፈጸምብን ነው ሲሉ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መግባታቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ፤ የሽብር ቡድኑ በቅርብ ርቀት…

በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ዳግም ወረራ እና ጥቃት ሊፈጸምብን ነው ሲሉ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መግባታቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ፤ የሽብር ቡድኑ በቅርብ ርቀት…

በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ዳግም ወረራ እና ጥቃት ሊፈጸምብን ነው ሲሉ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መግባታቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ፤ የሽብር ቡድኑ በቅርብ ርቀት ያሉ ቀበሌዎችን ያለ ተኩስ መቆጣጠሩን በመግለጽ የድረሱልን ጥሪ አቅርበዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ዳግም ወረራ እና ጥቃት ሊፈጸምብን ነው ሲሉ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መግባታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የሽብር ቡድኑ በቅርብ ርቀት ያሉ ቀበሌዎችን ያለ ተኩስ መቆጣጠሩን በመግለጽ የድረሱልን ጥሪ አቅርበዋል። እንደ ነዋሪዎች አገላለጽ ሰኔ 11/2014 ከ1,500 በላይ ንጹሃን አማራዎችን በማንነታቸው ብቻ በአሰቃቂ መልኩ በጅምላ በፈጁበት በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ በተባለው ቀበሌ አሁንም ዳግማዊ ወረራ እና ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል ጠቁሟል። የድረሱልን ጥሪ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) የሚያቀርቡት ነዋሪዎች በአሁኑ ሰዓት በቶሌ ቀበሌ 750 አባዎራዎች በድምሩ ከ3,500 በላይ አማራዎች መኖራቸው ታውቋል። በጊምቢ ወረዳ ከቶሌ ቀበሌ በግምት በ5 ኪ/ሜትር ርቀት ያለችው ጆግር ቀበሌ ጥቅምት 23/2015 ከቀኑ 12 ሰዓት ገደማ ያለ ምንም የተኩስ ልውውጥ በኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን በቁጥጥር ስር መዋሏን የአሚማ ምንጮች አረጋግጠዋል። በምዕራብ ወለጋ ዞን የጊምቢ ወረዳ መስተዳድር ጥቅምት 22/2015 ከሌሊቱ 8 ሰዓት ጀምሮ በጆግር ቀበሌ የነበሩ ሚሊሾችን ለቃችሁ ውጡ ሲል በመደወሉ ቀድመው ጥለው መውጣታቸው ተገልጧል። የቶሌ አማራዎች እንደሚሉት በሁለት አቅጣጫ በከባድ የሽብር ቡድኑ ኃይል ከበባ ስር ይገኛሉ። የሽብር ቡድኑ አባላት:_ 1) ከቶሌ በስተ ሰሜን አቅጣጫ_ጨፌን ከያዙ ሰነባብተዋል። 2) በስተ ምዕራብ አቅጣጫ_ጆግርን ጥቅምት 23/2015 ያለተኩስ ልውውጥ እንዲይዙ ተደርጓል። 3) በስተ ደቡብ አቅጣጫ በኩል ደግሞ ጨዋቃ ዳበና ወንዝ ስለሞላ ወደ ጨዋቃ አልፎ ለመሄድ አይቻልም። ከነቀምት ወደ ጊምቢ የሚወስደው መንገድ በዲጋ ወረዳ አርጆ ጉደቱ መቃ ላይ በቡድኑ ከታገደ 3 ቀናት ተቆጥሯል። የጊምቢ ወረዳ በቶሌ ያለውን የፌደራል ፖሊስ ጥቅምት 23/2015 ማለዳ ላይ ወደ ዴዴሳ ተጠጋ በማለቱ ከቀደመው ጥቃት የተረፉ አማራዎችም አብረው ለመሸሽ ሲሞክሩ እንደገና ተደውሎ ተረጋጉ መባሉን ገልጸዋል። በጊምቢ ወረዳ በቡድኑ የተያዙ አካባቢዎች:_ 1) አባሲና_ጥቅምት 22/2015፣ 2) ጆግር_ጥቅምት 23/2015፣ 3) ማርች_ከተያዘ የቆዬ፣ 4) ጨፌ_ከተያዘ የቆዬ፣ 5) ጨዋቃ_የቶሌ አዋሳኝ በመቱ ዞን የተያዘ እና ውሃ ነው የሚለዬው፣ ከእነዚህም በተጨማሪ በሽብር ቡድኑ የተያዙ ሌሎች አካባቢዎች እንዳሉም ተሰምቷል። በመጨረሻም አሁን ላይ ምንም ዋስትና የለንም የሚሉት ነዋሪዎች አባካችሁ የሚመለከተው አካል መንገድ አስከፍቶ በመምጣት ከዳግም የዘር ፍጅት ይታደገን ሲሉ ተማጽነዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply