በምዕራብ ወለጋ ዞን ግንቢ ወረዳ ቶሌ በተባለ ቀበሌ ከሰሞኑ ኦነግ ሸኔ በእናትና ልጅ ላይ የፈፀመውን የጭካኔ ግድያን፣ዝርፊያን እና ቃጠሎን ተከትሎ  የሚፈናቀሉ አማራዎች ቁጥር እያሻቀበ መሆኑ…

በምዕራብ ወለጋ ዞን ግንቢ ወረዳ ቶሌ በተባለ ቀበሌ ከሰሞኑ ኦነግ ሸኔ በእናትና ልጅ ላይ የፈፀመውን የጭካኔ ግድያን፣ዝርፊያን እና ቃጠሎን ተከትሎ የሚፈናቀሉ አማራዎች ቁጥር እያሻቀበ መሆኑ…

በምዕራብ ወለጋ ዞን ግንቢ ወረዳ ቶሌ በተባለ ቀበሌ ከሰሞኑ ኦነግ ሸኔ በእናትና ልጅ ላይ የፈፀመውን የጭካኔ ግድያን፣ዝርፊያን እና ቃጠሎን ተከትሎ የሚፈናቀሉ አማራዎች ቁጥር እያሻቀበ መሆኑን ነዋሪዎች ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራብ ወለጋ ዞን ግንቢ ወረዳ ቶሌ በተባለው ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ዘይነባ ሰይድ እና ልጃቸው ቶፊቅ እንድሪስ በቤታቸው ውስጥ ባሉበት ሁኔታ ኦነግ ሸኔ ብሎ ራሱን በሚጠራው ነፍሰ ገዳይ ቡድን ምሽት ላይ በጥይት የተገደሉ መሆኑን የአማራ ሚዲያ ማዕከል መዘገቡ ይታወሳል። ከዚህም በተጨማሪ በቶሌ ቀበሌ 14 የአማራ ቤቶች በጥይት የተደበደቡ መሆኑንና ይህን ተከትሎም ከ300 በላይ የሚሆኑ አማራዎች ህግ የሚያስከብርና ለደህንነታችን ዋስትና የሚሰጥ አካል አልተገኘም በሚል እየለቀቁ መውጣታቸው ተገልጧል። አሁንም ኦነግ ሸኔዎችና ተባባሪዎቹ ምሽት እና ሌሊት ላይ ጥይት በመተኮስ “እየመጣን ነው፤ ውጡ!” የሚል ማስፈራሪያ እየላኩ በመሆኑና በስጋትም ጭምር ቀየውን እየጣለ የሚወጣው አማራ ቁጥሩ እየጨመረ ነው ተብሏል። ከቶሌ ከተማ፣ከስልሳውና አካባቢው በህይወት ለመሰንበት ሲሉ ሀብት ንብረታቸውን እየጣሉ ለቀው የሚወጡ ተፈናቃይ አማራዎችም ወደ መተከል እና ነቀምት እየተጓዙ መሆኑ ተነግሯል። የግንቢ ወረዳም ሆነ የምዕራብ ወለጋ ዞን የመስተዳድር አካላትም ቀርበው እያነጋገሯቸውና ችግራቸውን እየፈቱ ባለመሆኑ ነው መፈናቀሉ የተባባሰው የሚሉት ነዋሪዎቹ የሚመለከተው የፌደራልም ሆነ የክልል መንግስት መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። በፅንፈኝነት የሚታወቁት ኦነጋዊያን የሌላ ብሄር ተወላጆችን ከአካባቢው በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ተፅዕኖ በመፍጠርና በማፅዳት ኦሮሚያ የሚባል ሀገር የመመስረት አላማ እንዳላቸው ይታወቃል። በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ ፅንፈኞች ከኦነግ ሸኔ ጋር በመተባበር በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ያሉ የሌላ ብሄር ተወላጆችን በማፅዳት የፅንፈኞች ህልምን ለማሳካት እየሰሩ ነው፤ ለዛ ነው በኦነግ ሸኔ ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ የማይወስዱት ሲሉ የሚወቅሱት በርካቶች ናቸው። በተያያዘ ወጣት መሀመድ የተባለ አማራም ከቶሌ ቀበሌ ስልሳው ከተባለ ጎጥ በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ታፍኖ ከተወሰደ አንድ ወር ቢያልፈውም እስካሁን ያለበትን አድራሻና ሁኔታ ለማወቅ አልተቻለም። ከሁለት ወራት በፊት በግንቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ጨፌ በተባለ ጎጥ ነዋሪ የሆኑት አቶ መሀመድ ሁሴን ለ5 ቀናት በኦነግ ሸኔ ከታገቱ በኋላ 100 ሽህ ብር፣ አቶ ያሲን ካሳ ደግሞ ከ3 ቀናት የእገታ ቆይታ በኋላ 60 ሽህ ብር በመክፈል የተለቀቁ መሆናቸው ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply