በምዕራብ ወለጋ  የደምቢዶሎ ከተማ ከንቲባ የሆኑት አቶ እያሱ በኦነግ ታጣቂወች መገደላቸው ተሰማ፡፡  /  አሻራ ሚዲያ  ህዳር፡-14/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር /… የደምቢዶሎ ከተማ ከንቲ…

በምዕራብ ወለጋ የደምቢዶሎ ከተማ ከንቲባ የሆኑት አቶ እያሱ በኦነግ ታጣቂወች መገደላቸው ተሰማ፡፡ / አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-14/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር /… የደምቢዶሎ ከተማ ከንቲ…

በምዕራብ ወለጋ የደምቢዶሎ ከተማ ከንቲባ የሆኑት አቶ እያሱ በኦነግ ታጣቂወች መገደላቸው ተሰማ፡፡ / አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-14/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር /… የደምቢዶሎ ከተማ ከንቲባ አቶ እያሱ ቀነኣ ትናት ዕሁድ ሕዳር 13 ቀን 2013 ዓም በኦነግታጣቂወች በጥይት ተመተው መውደቃቸው ተገልጿል። አቶ እያሱ ነፍሳቸው ሳትወጣ ለህክምና የተወሰዱ ቢሆንም አሁን ከደምቢዶሎ በደርሰን መረጃ መሰረት አቶ እያሱ ማረፋቸውን ታውቋል። በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ጋሲ በሚባል ቀበሌ በትላንትናው ዕለት በርካታ የኦነግ አባላት በመግባት የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ሲያወድሙ መዋላቸውንም ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት በምዕራብ ወለጋ ላይ ትኩረት ሊያደርግ ይገባልም ብለዋል፡፡ በአሁኑ ስዓትም በምዕራብ ወለጋ በውጥረት ላይ እንደምትገኝና ህዝቡም ችግር ውስጥ እንደገባ ጠቁመዋል፡፡ የኦነግ አጥፊው ቡድን ባሳለፍነው ወር ጊምቢ ወረዳ በንጹሃን የአማራ ልጆች ላይ ጭፍጨፋ የፈጸሙ መሆናቸውንም አውስተዋል። በመጨረሻም ይህ አዝማሚያ በንጹሃኑ ላይ ከፍተኛ ፍራቻን ፈጥሯል ስለዚህ መንግስት ይድረስልን ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ዘጋቢ፡-ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply